የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳግም 11

11
መታዘዝ የሚያስገኘው ጥቅም
1 # ዘፍ. 26፥5፤ 1ነገ. 2፥3። “እንግዲህ ጌታ አምላክህን ውደድ፤ ግዴታውን፥ ሥርዓቱን፥ ሕጉንና ትእዛዙን ሁልጊዜ ጠብቅ። 2#ዘዳ. 4፥9፤ 6፥20-25።የጌታ አምላክህን ተግሣጽ ይኸውም ግርማውን፥ ብርቱ እጁንና የተዘረጋች ክንዱን ያዩትና የተለማመዱት ልጆቻችሁ ሳይሆኑ እናንተ እንደ ሆናችሁ ዛሬ አስታውሱ፤ 3#ዘዳ. 6፥22፤ 7፥18-19፤ 26፥8፤ 29፥1-2፤ 34፥11፤ መዝ. 78፥42-51።በግብጽ መካከል፥ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፥ 4#ዘፀ. 14፥26-31፤ 15፥1-10፤ ኢያ. 24፥6-7፤ መዝ. 78፥53፤ 106፥9-11።በግብፃውያን ሠራዊት፥ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፥ እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ በቀይ ባሕር ውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውና ጌታ ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤ 5ከምድረ በዳው አንሥቶ እዚህ እስከምትደርሱ ድረስ፥ ለእናንተ ያደረገላችሁን፤ 6#ዘኍ. 16፥1-35፤ መዝ. 106፥16-17።የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንና አቤሮንን ከነቤተሰቦቻቸው፥ ከነድንኳናቸውና ከነእንስሳታቸው በመላው እስራኤል መካከል ምድር እንዴት አፏን ከፍታ እንደዋጠቻቸው እነርሱ አላዩም። 7የእናንተ ዐይኖች ግን ጌታ ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል።”
8 # ዘዳ. 5፥33፤ 6፥1-3። “ስለዚህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደምትወርሷት ምድር ለመግባትና ለመያዝ ብርታት እንድታገኙ፥ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤ 9ለአባቶቻቸውና ለዘሮቻቸው ጌታ ሊሰጣቸው በማለላቸው፥ በዚያች ማርና ወተት በምታፈሰው ምድር ረጅም ዕድሜ ትኖሩ ዘንድ፥ 10የምትገባባት ምድር እንደ ወጣህባትና ዘርህን ዘርተህባት በእግርህ ውሃ እንዳጠጣሃት የአትክልት ቦታ እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። 11#ዘዳ. 8፥7-10።ዮርዳኖስን ተሻግረህ ልትወርሳት ያለችው ምድር ግን፥ ከሰማይ ዝናብ የምትጠጣ፥ ተራሮችና ሸለቆች ያሉባት ምድር ናት። 12ይህች ምድር ጌታ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፥ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የጌታ የአምላክህ ዐይን ምንጊዜም የማይለያት ናት።”
13 # ዘዳ. 7፥12-14፤ 10፥12-13፤ 28፥1-14፤ ዘሌ. 26፥3-5፤ መዝ. 104፥14፤ ኤር. 5፥24። “ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥ 14እህልህን፥ ወይንህንና ዘይትህን እንድትሰበስብ የበልጉንና የክረምቱን ዝናብ በምድርህ ላይ በየወቅቱ አዘንባለሁ። 15በሜዳ ላይ ለከብቶችህ ሣር እሰጣለሁ፤ አንተም ትበላለህ፤ ትጠግባለህም። 16#ዘዳ. 4፥25-27፤ 6፥14-15፤ 28፥15-68።ተጠንቀቁ! ተታላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ፤ እንዳትሰግዱላቸውም።#ዘዳ. 5፥6-10፤ 7፥1-6፤ 1ነገ. 8፥35-36። 17የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።”
18 # ዘዳ. 6፥6-9። “እነዚህን ቃሎቼን፥ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፥ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ። 19ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፥ መንገድ ስትሄድ፥ ስትተኛና ስትነሣ ስለዚህ አጫውታቸው። 20በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው፤ 21ይህን ካደረጋችሁ፥ ጌታ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።”
22 # ዘዳ. 7፥1፤ 9፥1-3፤ 10፥12-13። “አምላካችሁን ጌታን ትወዱ ዘንድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፥ 23ከዚያም ጌታ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፥ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ። 24#ዘዳ. 1፥7፤ ዘፀ. 23፥31፤ ኢያ. 1፥3።በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል። 25#ዘዳ. 2፥25፤ 7፥23-24፤ ዘፀ. 23፥27።ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ ጌታ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል።”
26 # ዘዳ. 28፥1-68፤ 30፥1፤15-20፤ ዘሌ. 26፥3-45። “እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤ 27በረከቱ ዛሬ የምሰጣችሁን የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ስትፈጽሙ ሲሆን፥ 28#ዘዳ. 32፥16-18።መርገሙ ደግሞ፥ የጌታ የአምላካችሁን ትእዛዞች የማትፈጽሙ፥ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።”
29 # ዘዳ. 27፥12-13፤ ኢያ. 8፥30-35። “ልትወርሳት ወደምትሄድባት ምድር ጌታ አምላክህ በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ። 30#ዘፍ. 12፥6፤ 35፥4።እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊትለፊት፥ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን? 31አምላካችሁ ጌታ በሚሰጣችሁ ምድር ትገቡባትና ትወርሷት ዘንድ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ስለሆነ፥ ምድሪቱን ወርሳችሁ በምትኖሩባት ጊዜ፥ 32ዛሬ በፊታችሁ እኔ ያስቀመጥኳቸውን ሥርዓቶችና ሕጎች ሁሉ ለመፈጸም ትጉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ