ኦሪት ዘዳግም 12
12
ከአሕዛብ አምልኮ ስለ መራቅ
1 #
ዘዳ. 4፥44-45። “የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ፥ እንድትወርሷት በሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ ሁሉ፥ በጥንቃቄ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው። 2#ዘዳ. 5፥7-10፤ ዘፀ. 20፥24-26፤ 2ነገ. 18፥3-6፤ 22፤ 23፥4-9።ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው አሕዛብ በረጅሙ ተራሮች፥ በኰረብቶችና በእያንዳንዱ ዛፍ ሥር አማልክታቸውን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።#ዘዳ. 7፥5፤24-25፤ ዘፀ. 23፥23-24፤ 34፥11-14፤ ዘኍ. 33፥51-52፤ መሳ. 17፥3-5፤ 1ነገ. 12፥28-30፤ 14፥22-24፤ 2ነገ. 16፥4፤ 17፥7-12፤ ኤር. 2፥20፤ 3፥6-10፤ ሆሴዕ 4፥12-13። 3መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፤ የማምለኪያ አምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የ ‘አሼራ’ ምስል ዐምዶቻቸውን በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን ጣዖቶች ቆራርጣችሁ ጣሉ፤ ስማቸውንም ከእነዚያ ስፍራዎች ላይ አጥፉ።”
4“በዚያ ዓይነት አካሄድ ጌታ አምላካችሁን አታምልኩ። 5#ዘዳ. 12፥11-12፤ 14፥22-26፤ 15፥19-20፤ 16፥2፤ 6፤ 10—11፤ 14—15፤ 26፥2።ነገር ግን ጌታ አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆነው፥ በነገዶቻችሁ መካከል የሚመርጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደ እዚያም ስፍራ ትሄዳላችሁ።#2ሳሙ. 7፥13፤ 1ነገ. 8፥16-21፤27-30። 6#ዘዳ. 14፥22-27፤ 15፥19-23፤ 23፥21-23፤ 26፥12-15፤ ዘሌ. 1፥3-17፤ 3፥1-17፤ 6፥2-6፤ 7፥29-36፤ 27፥1-8፤ ዘኍ. 15፥18-21፤ 28፥2-8፤ 30፥2-15፤ አሞጽ 4፥4-5፤ 5፥22።እዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ ስእለቶቻችሁንና የፈቃዳችሁን ስጦታዎች፥ የከብት መንጋችሁን እና የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አቅርቡ። 7#ዘዳ. 12፥12፤18-19፤ 14፥26-27፤ 15፥20፤ 16፥11፤ 14፤ 26፥11።በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”
8 #
ዘዳ. 6፥18፤ 12፥28፤ መሳ. 17፥6፤ 21፥25። “ዛሬ እንደምናደርገው ሁሉ፥ እያንዳንዱ የሚመስለውን እንዳደረገ አታድርጉ፤ 9ምክንያቱም ማረፊያ ወደ ሆነውና ጌታ አምላካችሁ ወደ የሚሰጣችሁ ርስት ገና አልደረሳችሁም። 10#ዘዳ. 3፥18-20፤ 11፥22-25፤ ኢያ. 23፥1፤ 2ሳሙ. 7፥1፤ 1ነገ. 5፥17-18፤ 8፥56።ይሁን እንጂ ዮርዳኖስን ስትሻገሩና ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ስትቀመጡ፥ ያለ ሥጋት እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል። 11#ዘዳ. 12፥5-7፤ 14፥22-26፤ 15፥19-20፤ 16፥2፤ 6፤ 10—11፤ 14—15፤ 26፥2።ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ። 12እዚያም እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም የራሳቸው ድርሻ ወይም ርስት የሌላቸው በየከተሞቻችሁ የሚኖሩት ሌዋውያን በጌታ በአምላካችሁ ፊት ሐሤት አድርጉ።”
ትክክለኛ የአምልኮ ስፍራ
13 #
ኢያ. 22፥10-34። “የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በፈለግኸው ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። 14ከነገዶችህ መካከል በአንዱ፥ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ ብቻ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህን አቅርብ፤ እዚያም እኔ የማዝህን ሁሉ ጠብቅ።”
15 #
ዘዳ. 12፥20-22፤ 15፥22፤ ዘሌ. 7፥19-21። “ሆኖም ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ መጠን፥ በየትኛውም ከተማህ፥ እንስሳትህን ሚዳቋም ሆነ ድኩላ ዐርደህ የምትፈልገውን ያህል ሥጋ ብላ። በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነም ሆነ ያልሆነ ሰው ከዚሁ ሥጋ ሊበላ ይችላል። 16#ዘዳ. 12፥23-27፤ 15፥23፤ ዘፍ. 9፥4፤ ዘሌ. 3፥17፤ 17፥10-14፤ 19፥26፤ 1ሳሙ. 14፥31-35።ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። 17የእህልህን፥ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አሥራት፥ ወይም የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት፥ ወይም ለመስጠት የተሳልኸውን ወይም የፈቃድህን ስጦታ፥ ወይም የእጅህን ስጦታ፥ በከተሞችህ ውስጥ መብላት የለብህም። 18አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፤ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል። 19#ዘዳ. 14፥27።በምድርም ላይ በምትኖርበት ጊዜ ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትለው ተጠንቀቅ።”
20 #
ዘሌ. 17፥3-9። “አምላክህ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህ፥ ሥጋ አምሮህ፥ ‘ሥጋ መብላት እፈልጋለሁ’ በምትልበት ጊዜ፥ ያሰኘህን ያህል ሥጋ መብላት ትችላለህ።#ዘዳ. 19፥8፤ ዘፍ. 28፥14፤ ዘፀ. 34፥24። 21ስሙን ለማኖር ጌታ እግዚአብሔር የመረጠው ስፍራ ከአንተ እጅግ የራቀ ከሆነ፥ ባዘዝሁህ መሠረት ከቀንድ ከብትህ፥ ከበግና ከፍየል መንጋህ እንስሳት ማረድ ትችላለህ፤ በከተሞችህ ውስጥ የምትፈልገውን ያህል መብላት ትችላለህ። 22ሚዳቋ ወይም ድኩላ እንደሚበላ አድርገህ ብላ፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ መብላት ይችላል። 23#ዘዳ. 12፥16፤ 15፥23፤ ዘፍ. 9፥4፤ ዘሌ. 3፥17፤ 17፥10-14፤ 19፥26፤ 1ሳሙ. 14፥31-35።ደሙን ግን እንዳትበላ ተጠንቀቅ፤ ደም ሕይወት ስለ ሆነ፥ ሥጋን ከነሕይወቱ አትብላ። 24ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። 25በጌታ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላቸው አትብላው። 26ነገር ግን የተቀደሱ ነገሮችህን ለመስጠት የተሳልሃቸውን ሁሉ ይዘህ ጌታ ወደ የሚመርጠው ስፍራ ሂድ። 27#ዘሌ. 17፥11።የሚቃጠል መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንም ደሙንም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ። 28#ዘዳ. 4፥40፤ 5፥29፤ 6፥2-3፤17-18፤ 12፥25።በአምላክህ በጌታ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘለዓለም መልካም እንዲሆንላችሁ፥ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።”
ለጣዖት አምልኮ እንደማይገባ
29 #
ዘዳ. 7፥1-5፤ 25፤ ዘፀ. 23፥33፤ 34፥12፤ መሳ. 2፥2-3። “የምትወሯቸውንና የምታስለቅቋቸውን አሕዛብ አምላካችሁ ጌታ ከፊታችሁ ያስወግዳቸዋል፤ ባስወጣችኋቸውና በምድራቸው በተቀመጣችሁ ጊዜ ግን፥ 30ከፊትህ ከጠፉ በኋላ፥ ‘እነዚህ ሕዝቦች አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ’ ብለህ በመጠየቅ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። 31#ዘዳ. 18፥10፤ ዘሌ. 18፥21፤ 20፥2-5፤ 2ነገ. 3፥27፤ 16፥3፤ 21፥6፤ 23፥10፤ ኤር. 7፥31፤ 19፥5።አምላክህን ጌታ በእነርሱ መንገድ ፈጽሞ አታምልክ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን ሲያመልኩ ጌታ የሚጸየፈውን ሁሉንም ዓይነት ነገር ያደርጋሉና፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን እንኳን ለአማልክታቸው መሥዋዕት አድርገው ያቃጥላሉ።”
32 #
ዘዳ. 4፥2፤ ራእ. 22፥18፤19። “እኔ ያዘዝሁህን ሁሉ ጠብቅ፤ በእርሱ ላይ ምንም አትጨምር፤ ከእርሱም አንዳች ነገር አትቀንስ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ