የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳግም 13

13
1“ከመካከልህ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ተነሥቶ ምልክት ወይም ድንቅ አደርጋለሁ ቢልህ፥ 2#ዘዳ. 6፥4፤14-15፤ 17፥2-7።የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፥ ‘አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው’ ቢልህ፥ 3አምላካችሁን ጌታ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ ጌታ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም አላሚውን አትስሙ። 4#ዘዳ. 8፥2፤ 16።አምላካችሁን ጌታን ተከተሉት፤ ፍሩት፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ታዘዙት፤ አገልግሉት፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ። 5#ዘዳ. 6፥4-5፤ 10፥20፤ 11፥22።ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በጌታ ላይ ሊያስታችሁ ተናግሮአልና፥ አምላካችሁ ጌታ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፥ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።”
6 # ዘዳ. 17፥7፤ 12፤ 19፥19፤ 21፥21፤ 22፥21-22፤ 24፤ 24፥7፤ ኤር. 28፥16፤ 29፥32። “የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥ 7አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን በቅርብም ሆነ በሩቅ፥ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላው ድረስ በዙሪያህ ያሉትን የአሕዛብ አማልክት እናምልክ ቢልህ፥ 8እሺ አትበለው፤ ወይም አታዳምጠው፤ አትራራለት፤ አትማረው፤ ወይም አትሸሽገው። 9#ዘዳ. 7፥16፤ 19፥13፤ 21፤ 25፥12።ያለ ማመንታት ግደለው፤እርሱንም ለመግደል በመጀመሪያ የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይነሣ። 10#ዘዳ. 17፥5-7፤ 21፥21፤ 22፥20-24፤ ኢያ. 7፥25-26፤ 1ነገ. 21፥13-14።የባርነት ምድር ከሆነው ከግብጽ ካወጣህ ከጌታ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ፈልጎአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። 11ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም በማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አይደረግም።”
12 # ዘዳ. 17፥13፤ 21፥21። “አምላክህ ጌታ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፥ 13ክፉ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፥ ‘ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ’ በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፥ 14ጉዳዩን አጣራ፤ መርምር፤ በሚገባም ተከታተል፤ ነገሩ እውነት ሆኖ ከተገኘና ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፥ 15#ዘዳ. 17፥4፤ 19፥18።በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው፤ ከተማይቱን ከነ ሕዝቧና ከነ ቀንድ ከብቷ ፈጽሞ ደምስስ። 16#ዘዳ. 20፥16-18፤ ኢያ. 6፥17፤ 24፤ 7፥25-26፤ 8፥28።በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፥ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ ለጌታ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘለዓለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ። 17ጌታ ከብርቱ ቁጣው እንዲመለስ እርም ነገሮች በእጅህ አይገኝ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥር ህን ያበዛዋል። 18ይህም የሚሆነው፥ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ከጠበቅህ፥ በጌታ በአምላክህ ፊት ትክክል የሆነውን ካደረግህ፥ የጌታ የአምላክህን ቃል ከሰማህ ነው።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ