ኦሪት ዘዳግም 14
14
የተከለከለ የአሕዛብ ልምድ
1 #
ዘዳ. 32፥5-6፤18-20፤ ዘሌ. 19፥27-28፤ 21፥5፤ መዝ. 103፥13፤ ኢሳ. 1፥2፤ 4፤ 30፥1፤ ኤር. 3፥14፤ 19፤ 22፤ 16፥6፤ 31፥9፤ 20፤ 41፥4-5፤ ሆሴዕ 2፥1፤ 11፥1-4። “እናንተ የጌታ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትቦጭቁ፤ የጭንቅላታችሁን ጠጉር አትላጩ፤ 2#ዘዳ. 7፥6፤ ዘፀ. 19፥5-6።ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለጌታ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንድትሆንለት ጌታ በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ አንተን መርጦሃል።
የሚበሉና የማይበሉ እንስሶች
3 #
የሐዋ. 10፥14። “ርኩስ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ። 4#ዘሌ. 11፥2-23።የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፤ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፥ 5አጋዘን ሚዳቋ፥ ቦራይሌ፥ የሜዳ ፍየል፥ ዋላ፥ ድኩላንና ብሖር፤ 6ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፥ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ። 7ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፥ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ቢያመሰኩሁም፥ ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው። 8ዐሣማም፥ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩህ፥ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥምባቸውንም አትንኩ።
9“በውኆች ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው፥ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ። 10ክንፍና ቅርፊትም የሌለውን ግን አትብሉ፤ ለእናንተ ርኩስ ነው።
11“ንጹሕ የሆነውን ወፍ ሁሉ ትበላላችሁ። 12የሚከተሉትን ግን አትበሉም፦ ንስር፥ ገዴ፥ ዓሣ አውጪ፥ 13ጭልፊት፥ ጭላትና መሰሎቻቸው፥ 14ቁራና መሰሎቹ፤ 15ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቋልና መሰሎቹ፥ 16ጉጉት፥ ጋጋኖ፥ የውኃ ዶሮ፥ 17ይብራ፥ ጥንብ አንሣ አሞራ፥ እርኩም፥ 18ሽመላ፥ ሳቢሳና መሰሎቹ፥ ጅንጅላቴ ወፍና የሌሊት ወፍ ናቸው። 19ክንፍ ያላቸው ጥቃቅን ነፍሳት ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው፤ እነርሱን አትብሏቸው። 20ንጹሕ የሆነውን ማናቸውንም ክንፍ ያለውን ፍጡር ትበላላችሁ።
21 #
ዘፀ. 22፥30፤ 23፥19፤ 34፥26፤ ዘሌ. 17፥15፤ 22፥8፤ ሕዝ. 44፥31። “አንተ ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ እንዲበላ ልትሰጠው ትችላለህ፤ ወይም ለውጭ አገር ሰው ልትሸጠው ትችላለህ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
የአሥራት አወጣጥ ሕግ
22 #
ዘፍ. 14፥20፤ 28፥22፤ ዘሌ. 27፥30-33፤ ዘኍ. 18፥21-32፤ 1ሳሙ. 8፥15፤ 17፤ 2ዜ.መ. 31፥2-19፤ ነህ. 12፥44፤ አሞጽ 4፥4። “በየዓመቱ ከእርሻህ ከምታገኘው ምርት ከዐሥር አንዱን እጅ ለይተህ አስቀምጥ። 23#ዘዳ. 12፥5-7፤11-12፤17-18፤ 15፥19-20።ምንጊዜም ጌታ እግዚአብሔርን ማክበር ትማር ዘንድ፥ የወይን ጠጅና የዘይትህን አሥራት፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ስፍራ፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ። 24#ማር. 11፥15፤ ዮሐ. 2፥13-14።ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ፥ መንገዱ ቢርቅብህና ጌታ አምላክህ የስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ የሚመርጠው ስፍራ ከአንተ እጅግ ከመራቁ የተነሣ አሥራትህን ወደ እዚያ ቦታ ማድረስ ካልቻልክ፥ 25አሥራትህን በብር ለውጥ፤ ብሩንም ይዘህ ጌታ አምላክህ ወደ መረጠው ስፍራ ሂድ። 26#ዘዳ. 12፥7።በብሩም ደስ ያለህን ሁሉ ማለትም በሬና በግ፥ የወይን ወይም የብርቱ መጠጥ ወይም የምትሻውን ሁሉ ግዛበት። ከዚያም አንተና ቤተሰብህ በጌታህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላዋለህ፤ አንተና ቤተሰብህም ሐሤትም ታደርጋላችሁ። 27#ዘዳ. 12፥12፤ 19።በከተሞችህ የሚኖሩ ሌዋውያን ድርሻ ወይም ርስት ስለ ሌላቸው እነርሱን ችላ አትበል።
28 #
ዘዳ. 26፥12-15። “በየሦስት ዓመቱም መጨረሻ የዚያን ዓመት ሰብል አሥራት በሙሉ አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች። 29ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፥ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፥ አንተንም አምላክህ ጌታ በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 14: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ