ኦሪት ዘዳግም 16
16
የፋሲካ በዓል
1 #
ዘፀ. 12፥2—13፥10፤ 23፥15፤ 34፥18፤ ዘሌ. 23፥5-8፤ ዘኍ. 28፥16-25፤ ኢያ. 5፥10-12፤ 2ነገ. 23፥21-23፤ 2ዜ.መ. 30፥1-27፤ 35፥1-19፤ ሕዝ. 45፥21-24። “አምላክህ ጌታ በአቢብ ወር ከግብጽ በሌሊት ስላወጣህ፥ የአቢብን ወር ጠብቅ፤ የአምላክህን የጌታ ፋሲካ አክብርበት። 2#ዘዳ. 12፥5፤ 11፤ 16፥6።ጌታ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለጌታ ለእግዚአብሔር ፋሲካ አድርገህ ሠዋ። 3#ዘፀ. 12፥34፤ 39፤ 13፥6-7፤ 34፥18።የቦካውን ቂጣ ከእርሱ ጋር አትብላ፥ ከግብጽ አገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብጽ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ ይህን ቂጣ፥ እርሱም የመከራን እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ። 4በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቆይ አታድርግ።
5“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ በማናቸውም ከተማ ፋሲካን መሠዋት አይገባህም፤ 6#ዘዳ. 12፥5፤ 11፤ 16፥2።ነገር ግን አምላክህ ጌታ ለስሙ መጠሪያ በመረጠው ስፍራ ብቻ፥ ፀሐይ ስትጠልቅ ከግብጽ በወጣህበት ቀን የወጣህበትን ሰዓት በመጠበቅ በዚያ ፋሲካን ሠዋ። 7ሥጋውን ቀቅለህ አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ቦታ ብላው፤ በማግስቱ ወደ ድንኳኖችህ ተመለስ። 8#ዘፀ. 13፥6፤ ዘሌ. 23፥36፤ ዘኍ. 29፥35፤ ኢሳ. 1፥13፤ አሞጽ 5፥21።ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለጌታ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።
የመከር በዓል
9 #
ዘፀ. 23፥16፤ 34፥22፤ ዘሌ. 23፥15-21፤ ዘኍ. 28፥26-31። “እህልህን ማጨድ ከምትጀምርበት ዕለት አንሥቶ ሰባት ሳምንት ትቆጥራለህ፤ 10ከዚያም በኋላ ጌታ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን፥ በፈቃድህ የምታመጣውን ስጦታ በማቅረብ የመከር በዓል አምላክህ ጌታን አክብር። 11#ዘዳ. 12፥5-7፤ 11—12፤ 18።አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፥ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች ጌታ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ። 12አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክ አስታውስ፤ ይህንንም ሥርዓት በጥንቃቄ ጠብቅ።
የዳስ በዓል
13 #
ዘዳ. 31፥10-13፤ ዘፀ. 23፥16፤ 34፥22፤ ዘሌ. 23፥34-43፤ ዘኍ. 29፥12-38፤ 1ነገ. 8፥2፤62-66፤ ዕዝ. 3፥4፤ ነህ. 8፥14፤ ሕዝ. 45፥25። “ከአውድማህና ከመጥመቂያህ ፍሬህን በሰበሰብህ ጊዜ የዳስ በዓል ሰባትን ቀን ትጠብቃለህ። 14#ዘዳ. 16፥11።አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባርያህና ሴት ባርያህ፥ በአገርህም ደጅ ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሀ አደግና መበለትም በበዓል ደስ ይበላችሁ። 15አምላክህ ጌታ በፍሬህ ሁሉ በእጅህም ሥራ ሁሉ ይባርክሃልና ጌታ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለጌታ ሰባት ቀን በዓል ታደርጋለህ፥ አንተም ፈጽሞ ደስ ይልሃል።
16 #
ዘዳ. 12፥7፤ 16፥11፤ 14፤ ዘፀ. 23፥14-15፤ 17፤ 34፥23-24፤ 2ዜ.መ. 8፥13። “በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ። 17አምላክህ ጌታ በረከት እንደሰጠው መጠን እያንዳንዱ ሰው እንደ ችሎታው ይስጥ።
ስለ ፍርድ አሰጣጥ
18 #
ዘዳ. 1፥13-17፤ 17፥8-13፤ 19፥17፤ 21፥5፤ ዘፀ. 18፥13-26፤ 2ዜ.መ. 19፥5-11። “አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ። 19#ዘዳ. 1፥16-17፤ 10፥17-18፤ ዘፀ. 23፥2-3፤6-8፤ ዘሌ. 19፥15፤ ምሳ. 17፥23፤ 18፥5፤ 24፥23፤ ኢሳ. 1፥23፤ ሚክ. 7፥3፤ ዮሐ. 7፥24፤ ያዕ. 2፥9።ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦም አትቀበል። 20በሕይወት እንድትኖርና ጌታ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ ትክክለኛ፥ እውነተኛውንም ፍርድ ብቻ ተከተል።
የተከለከሉ አምልኮዎች
21 #
ዘዳ. 5፥7-10፤ 6፥4-5፤ 12፥29—14፥2፤ ዘዳ. 7፥5፤ ዘፀ. 34፥13፤ 1ነገ. 14፥15፤ 2ነገ. 23፥6፤ 15፤ 2ዜ.መ. 33፥3። “ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በጌታ መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል። 22ጌታ እግዚአብሔርም የሚጠላውን የማምለኪያ ሐውልት ለአንተ አታቁም።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 16: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ