ኦሪት ዘዳግም 19
19
የመማጸኛ ከተሞች
1 #
ዘዳ. 4፥41-43፤ ዘፀ. 21፥12-14፤ ዘኍ. 35፥9-34፤ ኢያ. 20፥1-9። “አምላክህ ጌታ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ ጌታ እግዚአብሔር በሚደመስሳቸውና አንተም እነርሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጥበት ጊዜ፥#ዘዳ. 6፥10-11፤ 12፥29። 2አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር አማካይ ስፍራ፥ ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ። 3ሰው የገደለ ሁሉ እንዲሸሽባቸው አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር መንገዶችን ሠርተህ፥ በሦስት ትከፈፍላለህ። 4በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመግባት ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው። 5አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊቆርጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፥ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፥ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል። 6አለበለዚያ በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና፥ መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል። 7ሦስት ከተሞችን እንድትለይ ያዘዝሁህ በዚሁ ምክንያት ነው።
8 #
ዘዳ. 11፥22-25፤ 12፥20፤ ዘፍ. 15፥18-21፤ 28፥14፤ ዘፀ. 23፥31። “ለአባቶችህ በመሐላ በገባላቸው ቃል መሠረት ጌታ እግዚአብሔር ወሰንህን ሲያሰፋውና ለእነርሱ በሰጣቸው መሠረት ምድሪቷን ሁሉ ሲሰጥህ፥ 9ጌታን እግዚአብሔርን እንድትወድና ምንጊዜም በመንገዱ እንድትሄድ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ እምትጠብቅ ከሆነ፥ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ። 10#ዘዳ. 21፥8-9።ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር የንጹሕ ሰው ደም እንዳይፈስና በሚፈሰውም ደም በደለኛ እንዳትሆን ይህን አድርግ።
11“ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፥ አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፥ ቢገድለውና፥ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥ 12የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። 13#ዘዳ. 13፥6፤ 9።አትራራለት፤ ነገር ግን መልካም እንዲሆንልህ የንጹሑን ደም በደል ከእስራኤል አስወግድ።
ድንበር ማፍረስ እንደማይገባ
14 #
ዘዳ. 27፥17፤ ኢዮብ 24፥2፤ ምሳ. 22፥28፤ 23፥10፤ ሆሴዕ 5፥10። “አምላክህ ጌታ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ።
ስለ ምስክሮች የተሰጠ መመሪያ
15 #
ዘዳ. 5፥20፤ ዘፀ. 20፥16፤ 23፥1። “በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ፥ አንድ ምስክር አይበቃም፤ ጉዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት።#ዘዳ. 17፥6፤ ዘኍ. 35፥30፤ ማቴ. 18፥16፤ ዮሐ. 8፥17፤ 2ቆሮ. 13፥1። 16ተንኰለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ቢከስ፥ 17#ዘዳ. 1፥17፤ 17፥8-12።ሁለቱም ወገኖች በጌታ ፊት፥ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። 18#ዳን. 13፥61-62።ፈራጆችም ጉዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፤ ያም ምስክሩ በወንድሙ ላይ የሐሰት ክስ አቅርቦ ከተገኘ፥#ዘዳ. 13፥15፤ 17፥4። 19በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በእርሱ ላይ አድርጉበት፤ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ። 20#ዘዳ. 13፥11።የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከልህ ከቶ አይደገምም። 21#ዘፀ. 21፥23-25፤ ዘሌ. 24፥19-20፤ ማቴ. 5፥38።ዓይንህም አትራራለት፥ ሕይወት በሕይወት፥ ዐይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ ይመለስ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 19: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ