የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳግም 24

24
ስለ ጋብቻና ፍች የተሰጠ ሕግ
1 # ዘዳ. 22፥13-19፤28-29፤ ሲራ. 7፥26፤ ኤር. 3፥1፤ ማቴ. 5፥31-32፤ 19፥3-9። “አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባት በኋላ፥ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት፥ የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። 2ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ብታገባ፥ 3ሁለተኛ ባሏም እንደዚሁ ጠልቷት የፍቺ ወረቀት በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ቢሰዳት ወይም ቢሞት፥ 4#ዘዳ. 7፥25-26።ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው። ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ።
ልዩ ልዩ ሕጎች
5 # ዘዳ. 20፥7። “አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፥ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ እቤቱ ይቆይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።
6“ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም ቢሆን፥ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና።
7 # ዘዳ. 13፥6፤ ዘፀ. 21፥16። “አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባርያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። በዚህ ዓይነት ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
8 # ዘሌ. 13፥1—14፥57። “የለምጽ ደዌን በተመለከተ ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡህን መመሪያ በትክክል ለመፈጸም ጥንቃቄ አድርግ። እኔ ለእነርሱ የሰጠሁትን ትእዛዝ በጥንቃቄ ተከተል። 9#ዘኍ. 12፥10-15።ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ ጌታ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ።
10“ማናቸውንም ነገር ለባልንጀራህ ስታበድር መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ለመቀበል ወደ ቤቱ አትግባ። 11አንተ ከውጭ ሆነህ ጠብቅ፤ ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ከቤት ያምጣልህ። 12ሰውየው ድኻ ከሆነ፥ መያዣውን ከአንተ ዘንድ አታሳድርበት። 13#ዘዳ. 6፥25፤ ዘፀ. 22፥25-26፤ አሞጽ 2፥8።መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርልሃል።
14 # ዘሌ. 19፥13፤ ኤር. 22፥13። “ድኻና ችግረኛ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድምህም ሆነ፥ ከከተሞችህ በአንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዘው፤#ዘዳ. 1፥16። 15#ዘዳ. 15፥9፤ ማቴ. 20፥1-16።የሠራበትን ሒሣብ በዕለቱ፥ ፀሓይ ሳትጠልቅ ክፈለው፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋል። ያለበለዚያ ወደ ጌታ ይጮኽና ኃጢአት ይሆንብሃል።
16 # ዘዳ. 7፥10፤ 2ነገ. 14፥6፤ 2ዜ.መ. 25፥4፤ ኤር. 31፥29-30፤ ሕዝ. 18፥20። “አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፥ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።
17 # ዘዳ. 10፥17-19፤ 15፥15፤ 24፥22፤ 27፥19፤ ዘፀ. 22፥21-24፤ 23፥9። “ለመጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈገው፤ የመበለቲቱንም መደረቢያ መያዣ አታድርግ። 18አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህና ጌታ እግዚአብሔር ከዚያ እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።
19 # ዘፀ. 23፥10-11፤ ዘሌ. 19፥9-10፤ 23፥22፤ ሩት 2፥1-23። “የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፥ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። 20የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። 21የወይን ተክልህን ፍሬ ስትሰበስብ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለስበት፤ የቀረውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። 22በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ