ኦሪት ዘዳግም 7
7
የተመረጠ ሕዝብ
1 #
ዘፀ. 23፥23-33፤ 34፥11-16፤ ዘኍ. 33፥51-56። “ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥#ዘዳ. 1፥7፤ ዘፍ. 10፥16-17፤ 13፥7፤ 15፥19-21፤ 23፥3-20፤ 34፥2፤ 30፤ 49፥29-30፤ ዘፀ. 3፥8፤ 23፥23፤ 33፥2፤ ዘኍ. 13፥29፤ ኢያ. 1፥4፤ 3፥10፤ 9፥1-7፤ 15፥63፤ 17፥15፤ 24፥11፤ መሳ. 1፥4-5፤ 3፥3፤ 5፤ 2ሳሙ. 5፥6-10፤ 1ነገ. 9፥20፤ ሕዝ. 16፥3፤ 45። 2#ዘዳ. 2፥34-35፤ 3፥6፤ 7፥26፤ 13፥16፤ 18፤ 20፥16-18፤ ዘፀ. 23፥32-33፤ 34፥12፤15፤ ኢያ. 9፥3-27፤ 10፥40፤ 11፥11-12፤ መሳ. 2፥2።ጌታ አምላክህም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና ድል በምትነሣበት ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፥ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፥ አትማራቸውም፥ 3#ዘፍ. 34፥9-10፤ ዘፀ. 34፥16፤ ኢያ. 23፥12-13፤ መሳ. 3፥5-6፤ 1ነገ. 11፥1-6።ከእነርሱም ጋር አትጋባ፥ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ፥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ፤ 4እኔን እንዳይከተል፥ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና፤ ያኔ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል። 5#ዘዳ. 12፥2-3፤29-31፤ 16፥21-22፤ ዘፀ. 34፥13፤ 2ነገ. 18፥4፤ 23፥4-24።ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም አድቅቁት፥ የእነርሱንም አሼራ#7፥5 የሴት አምላክ ምስል። ሰባብሩ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።
6 #
ዘዳ. 14፥2፤ 21፤ 26፥18-19፤ 32፥8-14፤ ዘፀ. 19፥5-6፤ መዝ. 135፥4፤ ሚል. 3፥17። “ለጌታ አምላክህ አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ፥ ጌታ አምላክህ ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንድትሆን መረጠህ። 7#ዘዳ. 10፥15።ጌታ የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ስለ በዛችሁ አይደለም፥ ይልቁንም እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ጥቂቶች ነበራችሁ፤ 8#ዘዳ. 5፥6፤ 9፥26፤ 13፥5፤ 15፥15፤ 21፥8፤ 24፥18፤ መዝ. 78፥42።ነገር ግን ጌታ ስለ ወደዳችሁ፥ አባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አወጣችሁ። 9#ዘዳ. 4፥31፤ 5፥9-10፤ 24፥16፤ ዘፀ. 20፥5-6፤ 34፥6-7፤ ዘኍ. 14፥18፤ ኤር. 31፥29-30፤ 32፥18-19፤ ሕዝ. 18፥1-24፤ ዮሐ. 9፥1-3።አንተም ጌታ አምላካችሁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ፥ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደሆነ እወቅ፤#ዘዳ. 5፥9-10፤ 7፥12፤ 32፥4፤ 1ነገ. 8፥23-24፤ ነህ. 1፥5፤ 9፥32፤ መዝ. 89፥1-2፤ 24፤ 28፤ 33—34፤ 98፥3፤ ኢሳ. 49፥7፤ 54፥10፤ 55፥3፤ ዳን. 9፥4፤ ዮናስ 4፥2፤ ሚክ. 7፥20። 10የሚጠሉትን በማጥፋት በፊታቸው ብድራት ይመልስባቸዋል፥ ለሚጠላው አይዘገይም፥ በፊቱ ብድራት ይመልስበታል። 11እንግዲህ እንድታደርገው ዛሬ ያዘዝኩህን ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፍርድ በጥንቃቄ ጠብቅ።
መታዘዝ የሚያስገኘው በረከት
12 #
ዘዳ. 15፥6፤ 28፥1-14፤ 30፥1-10፤ ዘፀ. 23፥22-33፤ ዘሌ. 26፥3-13። “እንዲህም ይሆናል፥ ይህችን ፍርድ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ጌታ አምላካችሁ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅር ለአንተም ይጠብቅልሃል፥ 13ይወድድህማል፥ ይባርክህማል፥ ያበዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ እንዲሁም የምድርህንም ፍሬ፥ እህልና ወይንህን፥ ዘይትህንም፥ በከብትም ብዛት በበግም መንጋ አብዝቶ ይባርክልሃል። 14ከሕዝቦች ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፥ ወንድ ይሁን ወይም ሴት በሰውህና በከብትህም ዘንድ መካን አይኖርብህም። 15ጌታም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፥ የምታውቀውንም ክፉውን የግብጽ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ግን ያመጣባቸዋል። 16#ዘዳ. 5፥7-10።ጌታ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ የሚጥላቸውን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋቸዋለህ፥ ዓይንህም አታዝንላቸውም፤ ወጥመድ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
17 #
ዘዳ. 1፥28-31፤ 3፥22፤ 4፥34፤37-38፤ 9፥1-3፤ 20፥1፤ 29፥2-3፤ ኢያ. 23፥3፤9-10። “በልብህም፦ ‘እነዚህ ሕዝቦች ከእኔ ይበልጣሉ፤ እንዴትስ አድርጌ አስወጣቸዋለሁ?’ ብለህ፥ 18ልትፈራቸው አይገባም፥ ነገር ግን ጌታ አምላካችሁ በፈረዖንና በግብጽ ሁሉ ያደረገውን አስብ፥ 19ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል። 20#ዘፀ. 23፥28።ደግሞም ጌታ አምላካችሁ የቀሩት ከፊትህም የተሸሸጉት እስኪጠፉ ድረስ ተርብ ይሰድድባቸዋል። 21ጌታ አምላክህ፥ ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ፥ በመካከልህ ነውና በእነርሱ የተነሣ ልትደናገጥ አይገባም። 22#ዘፀ. 23፥29-30፤ መሳ. 3፥1-6።ጌታ አምላካችሁ እነዚህን ሕዝቦች ጥቂት በጥቂት ከፊትህ ያስወጣቸዋል፤ የዱር አራዊት እንዳይበዙብህ፥ እነርሱን በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይቻልህም። 23#ዘዳ. 7፥2።ጌታ አምላካችሁ ግን እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ እስኪጠፉም ድረስ በታላቅ ሁከት ላይ ይጥላቸዋል። 24#ዘዳ. 11፥25፤ ኢያ. 12፥7-24።ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም ተቋቁሞህ በፊት ሊቆም አይችልም። 25#ዘዳ. 5፥8-9፤ 9፥21፤ ኢያ. 6፥18-19፤ 7፥1፤20-21፤ መሳ. 8፥24-27፤ 17፥2-4፤ 1ነገ. 15፥13፤ 2ነገ. 23፥4።የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።#ዘዳ. 12፥31፤ 17፥1፤ 18፥12፤ 22፥5፤ 23፥18፤ 24፥4፤ 25፥16፤ ምሳ. 6፥16፤ 15፥8-9፤ 26። 26እንደ እርሱም ለጥፋት የምትሆን እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ