ኦሪት ዘዳግም መግቢያ
መግቢያ
ኦሪት ዘዳግም፥ የእስራኤል ሕዝብ ለብዙ ጊዜ በምድረ በዳ ከተጓዙ በኋላ ወደ ከነዓን ለመግባት ጥቂት ሲቀራቸው በሞዓብ ምድር በቆዩበት ጊዜ ሙሴ በተከታታይ ያደረገላቸውን ንግግር የያዘ ነው።
በኦሪት ዘዳግም ተመዝግበው ከሚገኙት በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
1. ሙሴ ባለፉት አርባ ዓመቶች ውስጥ ስለ ተፈጸሙት ታላላቅ ድርጊቶች በማስታወስ ይናገራል፤ እግዚአብሔር በምድረ በዳ እንዴት እንደ መራቸው ሕዝቡን በማስታወስ፥ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዲሆኑና በቅንነት እንዲታዘዙት ያሳስባቸዋል።
2. ሙሴ ዐሥሩን ትእዛዞች እንደገና እየጠቀሰ በተለይ ስለ መጀመሪያው ትእዛዝ ፍች አብራርቶ እያስረዳ፥ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልኩ ያሳስባቸዋል፤ ከዚህም ጋር በማያያዝ እስራኤላውያን በተስፋይቱ ምድር ስለሚተዳደሩባቸው ልዩ ልዩ ሕጎች በድጋሚ እየጠቀሰ ያብራራል።
3. ሙሴ፥ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ምን ዓይነት እንደሆነ በመተርጐም፥ ሕዝቡ ለዚህ ቃል ኪዳን ያላቸውን ታማኝነት እንዲያድሱ ያስገነዝባቸዋል።
4. ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሪ በመሆን ይሾማል፤ ሙሴ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት የተቀኘውን መዝሙር ከዘመረና የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ ከባረከ በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በሞዓብ ምድር ይሞታል።
የመጽሐፉ ፍሬ ነገር እግዚአብሔር የሚወዳቸውንና የተመረጡትን ሕዝቡን ስለ ማዳኑና ስለ መባረኩ ይናገራል፤ ሕዝቡም የእግዚአብሔር በረከት ሳይለያቸው በሕይወት መኖር ይችሉ ዘንድ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ሁሉ በማስታወስ ዘወትር እግዚአብሔርን መውደድና ለእርሱም መታዘዝ እንደሚገባቸው ያስገነዝባል።
የመጽሐፉን ዋና ሐሳብ ከያዙ ጥቅሶች መሀል ዘዳግም 6፥4-6 ይገኝበታል። ኢየሱስ “ከትእዛዞች ሁሉ የምትበልጠው ታላቂቱ ትእዛዝ” ብሎ የተናገራቸውን ቃላት የሚገልጹ ጥቅሶች ናቸው። እነዚህም፦ “እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኃይልህ ውደድ” የሚሉት ቃላት ናቸው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ሀ. የመጀመሪያው የሙሴ ንግግር (1፥1—4፥49)
ለ. ሁለተኛው የሙሴ ንግግር (5፥1—26፥19)
1. ዐሥሩ ትእዛዞች (5፥1—10፥22)
2. ሕጎች፥ ደንቦችና ማስጠንቀቂያዎች (11፥1—26፥19)
ሐ. ወደ ከነዓን ከመግባታቸው በፊት የተሰጠ መመሪያ (27፥1—28፥68)
መ. የቃል ኪዳኑ መታደስ (29፥1—30፥20)
ሠ. የሙሴ የመጨረሻው ንግግር (31፥1—33፥29)
ረ. የሙሴ ሞት (34፥1-12)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ