ኦሪት ዘፀአት መግቢያ
መግቢያ
የስሙ ወይም የርእሱ ስያሜ እስራኤላውያን ከግብጽ ከመውጣታቸው ጋር የተያያዘ ነው። ፀአት፦ መውጣት፥ አወጣጥ እንደማለት ነው። ስለዚህ ኦሪት ዘፀአት ማለት የመውጣት ዜና፥ ሥርዓት፥ ደንብ፥ ሕግ ማለት ነው። ዘፀአት የሚለው አመጣጡ ከግሪክ የተወሰደና መውጣት፥ መለየት ማለት ነው (ዘፍ. 50፥24-25፥ ሉቃ. 9፥31፥ ዕብ. 11፥ 22)። ዘፀአት የሚለው ስያሜ በዕብራይስጥ ቋንቋ ከመጽሐፉ የመጀመሪያ ሁለት ቃላት (ኤሌህ ሽሞት) ትርጉሙም “ስሞች እነዚህ ናቸው” ማለት ነው። በኦሪተ ዘፍጥረት ለተነገረው ታሪክ ተከታይ መጽሐፍ ቢሆንም ለሕጉ ግን የመጀመሪያ መጽሐፍ ነው።
የኦሪት ዘፀአት ጠቅላላ ሐሳብ በምዕራፍ 19፥3-6 ተገልጧል። በተጠቀሱት ቁጥሮች የተገለጸው በሁለት ዋና ዋና ሐሳቦች ሊከፈል ይችላል። እነሱም፦ ግፈኞች በሆኑ ግብጻውያን ላይ የተደረገው የእግዚአብሔር ፍርድ (19፥4-5) እና ግፍና በደል ለተፈራረቀባቸው እስራኤላውያን የተሰጠው ነጻነትና ሕግ ናቸው (19፥4፤ 19፥5)። በአጠቃላይ ይህ መጽሐፍ እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ኃይል፥ በሙሴ መሪነት፥ ከግብጽ ባርነት ወጥተው ቀይ ባሕርን ተሻግረውና በሲና ተራራ ስር ሳሉ የሃይማኖት ሕግና የመንግሥት ሕግ ከተሰጣቸው በኋላ ራሳቸውን የቻሉ ነጻና የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ መባላቸውን በመጀመሪያው ክፍል ይተርካል፤ በ 2 ኛው ክፍል ደግሞ ስለተለያዩ ሕጎች ዘርዝሮ ያስረዳል። ሕጎቹም አሥሩ ትእዛዛት (ዘፀ. 20፥1-17)፥ የሕዝብ አስተዳደር ሕጎችና (ዘፀ. 21-23) እና የሃይማኖት ሕጎች ናቸው። ስለመገናኛው ድንኳን ሥርዓት፥ ስለ መሥዋዕትና ስለ ካህናት ሁኔታ የሚናገረው ሁሉ በዚህ ውስጥ ይካተታል (ዘፀ. 24-30)።
የኦሪት ዘፀአት ዓላማ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ እግዚአብሔር አምላክ፥ ስሙንና የስሙን ማንነት፥ የማዳን ኃይሉን፥ አመራሩን፥ ቃል ኪዳኑን፥ ሥርዓተ አምልኮውን ይዘረዝራል። እንዲሁም በማይታዘዙት ግብፃውያን እና የእግዚአብሔርን እርዳታ በሚጠብቁት እስራኤላውያን ላይ አስደናቂ ተአምራቱን እንዳሳየ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ነጻ መውጣት (1፥1—15፥21)
የእስራኤል ሕዝብ ባርነት በግብጽ (1፥1-22)
የሙሴ ልደትና እድገት (2፥1—4፥31)
ሙሴና አሮን በፈርኦን ፊት (5፥1—11፥10)
ፋሲካና ከግብጽ መውጣት (12፥1—15፥21)
ከቀይ ባሕር እስከ ሲና ተራራ የተደረገ ጉዞ (15፥22—18፥27)
ለእስራኤል ሕዝብ የተሰጠ ሕግና ቃል ኪዳን (19፥1—24፥18)
የተቀደሰው ድንኳንና የአምልኮ ሥርዓት (25፥1—40፥38)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ