ትንቢተ ሕዝቅኤል 2
2
የጥቅሉ ራእይ
1እርሱም፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ ከአንተ ጋር እንድነጋገር በእግርህ ቁም” አለኝ። 2ሲያናግረኝም መንፈስ ገባብኝ፥ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገረኝንም ሰማሁ። 3እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ። 4ፊታቸው የተኮሳተረና ልባቸውም የደነደነ ልጆች ናቸው፥ እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፥ አንተም እንዲህ በላቸው፦ “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤”
5እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ በመካከላቸው ነቢይ እንደ ነበረ ያውቃሉ። 6አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራ፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቃላቸውን አትፍራ፥ ፊታቸውንም አትፍራው። 7እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙም ባይሰሙም ቃሌን ትነግራቸዋለህ።
8አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፥ አፍህን ክፈት፥ የምሰጥህንም ብላ። 9#ራእ. 5፥1።ተመለከትሁም፥ እነሆ እጅ ወደ እኔ ተዘርግታ ነበር፥ እነሆ የመጽሐፍ ጥቅልል ነበረባት። 10በፊቴም ዘረጋው፥ በፊቱና በኋለውም ልቅሶ፥ ኃዘንና ዋይታም ተጽፎበት ነበር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ