ትንቢተ ሕዝቅኤል 25
25
በአሞን ላይ የተነገረ አዋጅ
1 #
ኤር. 49፥1-6፤ ሕዝ. 21፥28-32፤ አሞጽ 1፥13-15፤ ሶፎ. 2፥8-11። የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ አሞን ልጆች አድርገህ ትንቢት ተናገርባቸው። 3ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፦ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት ተማርከው በተወሰዱ ጊዜ እሰይ ብለሻልና፤ 4ስለዚህ እነሆ ርስት አድርጌ ለምሥራቅ ልጆች አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ እነርሱም በአንቺ ውስጥ ይሰፍራሉ፥ ማደሪያዎቻቸውንም በአንቺ ውስጥ ይሠራሉ፤ ፍሬሽን ይበላሉ ወተትሽንም ይጠጣሉ። 5ራባን የግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። 6ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ምድር ላይ በውስጥሽ ባለው ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሽ በእጅሽ አጨብጭበሻልና፥ በእግርሽም አሸብሽበሻልና፥ 7ስለዚህ እነሆ እጄን በአንተ ላይ ዘርግቻለሁ፥ እንዲበዘብዙህ ለሕዝቦች እሰጥሃለሁ፥ ከሕዝቦች እቆርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም እደመስስሃለሁ፤ አጠፋሃለሁም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃለህ።
በሞዓብ ላይ የተነገረ አዋጅ
8 #
ኢሳ. 15፥1—16፥14፤ 25፥10-12፤ ኤር. 48፥1-47፤ አሞጽ 2፥1-3፤ ሶፎ. 2፥8-11። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሞአብና ሴይር፦ እነሆ የይሁዳ ቤት እንደ ሌሎች ሕዝቦች ነው ብለዋልና፥ 9ስለዚህ እነሆ የሞዓብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከበኣልሜዎን፥ 10ከአሞን ልጆች ጋር ለምሥራቅ ልጆች እከፍታለሁ። ከእንግዲህ ወዲህ የአሞን ልጆች በሕዝቦች መካከል እንዳይታሰቡ ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ። 11በሞዓብም ላይ ፍርድ እሰጣለሁ። እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
በኤዶም ላይ የተነገረ አዋጅ
12 #
ኢሳ. 34፥5-17፤ 63፥1-6፤ ኤር. 49፥7-22፤ ሕዝ. 35፥1-15፤ አሞጽ 1፥11፤12፤ አብ. 1፥1-14፤ ሚል. 1፥2-5። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኤዶም በይሁዳ ቤት ላይ በቀል ተበቅሎአልና፥ በዚህም በደለኛ ሆኗል፥ በእነሱም ላይ ተበቅሎአልና፥ 13ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ። 14በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እንደ ቁጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ላይ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በፍልስጥኤማውያን ላይ የተነገረ አዋጅ
15 #
ኢሳ. 14፥29-31፤ ኤር. 47፥1-7፤ ኢዩ. 3፥4-8፤ አሞጽ 1፥6-8፤ ሶፎ. 2፥4-7፤ ዘካ. 9፥5-7። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍልስጥኤማውያን በቀልን አድርገዋልና፥ በዘወትርም ጠላትነት ያጠፉ ዘንድ በነፍሳቸው ንቀት ተበቅለዋልና 16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እጄን በፍልስጥኤማውያን ላይ እዘረጋለሁ፥ ከሊታውያንንም እቆርጣለሁ፥ የባሕሩንም ዳር የቀሩትን አጠፋለሁ። 17ቁጣ ከተሞላበት ቅጣት ጋር ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ፥ በቀሌን በእነሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 25: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ