ትንቢተ ሕዝቅኤል 48
48
የምድሪቱ አከፋፈል
1የነገዶቹ ስም ይህ ነው። ከሰሜን ወሰን በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ በደማስቆም ድንበር ባለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ካለው ከሰሜን ድንበር ይጀምራል። ወርዳቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 2ከዳን ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ አሴር አንድ ድርሻ ይኖረዋል። 3ከአሴር ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ንፍታሌም አንድ ድርሻ ይኖረዋል። 4ከንፍታሌም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ምናሴ አንድ ድርሻ ይኖረዋል። 5ከምናሴ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ኤፍሬም አንድ ድርሻ ይኖረዋል። 6ከኤፍሬም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ሮቤል አንድ ድርሻ ይኖረዋል። 7ከሮቤል ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሁዳ አንድ ድርሻ ይኖረዋል።
8ከይሁዳ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለምታቀርቡት መባ የሚሆን ድርሻ ይሆናል፤ ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል፥ ከድርሻዎቹ እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል። 9ለጌታ የምታቀርቡት መባ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱ ደግሞ አስር ሺህ ክንድ ይሆናል። 10ይህም ለካህናቱ የተቀደሰ መባ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል። የጌታ መቅደስም በመካከሉ ይሆናል። 11ሌዋውያን በሳቱ ጊዜ፥ እንደ ሳቱት እንደ እስራኤል ልጆች ላልሳቱት ሥርዓቴን ለጠበቁት ከሳዶቅ ልጆች ለተቀደሱት ካህናት ይሆናል። 12ከምድሪቱ መባ የተቀደሰው መባ ለእነርሱ ይሆናል፥ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል፤ በሌዋውያን ድንበር አጠገብ ይሆናል።
13ለሌዋውያኑ በካህናቱ ድንበር አጠገብ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ይሆናል፥ ርዝመቱ ሁሉ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። 14ለጌታ የተቀደሰ ስለሆነ ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡም፥ የምድሪቱንም በኵራት ወደ ሌላ አይተላለፍም።
15በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ለፊት አምስት ሺህ ወርድ ያለው የቀረ ስፍራ ለከተማይቱ ለጋራ ጉዳይዋ፥ ለመኖሪያና ለማሰማርያ ይሆናል፤ ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች። 16ልክዋም ይህ ነው፤ በሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በደቡብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምሥራቅ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምዕራብም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ይሆናል። 17ከተማይቱ ማሰማርያ ይኖራታል፤ በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብ በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅ በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆናል። 18በተቀደሰው መባ አጠገብ የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ ዐሥር ሺህ ወደ ምዕራብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። ይህም በተቀደሰው መባ አጠገብ ይሆናል። ምርቷም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል። 19ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማይቱን የሚያገለግሉ ያርሱታል። 20መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ የተቀደሰውን መባ ከከተማይቱ ድርሻ ጋር አራት ማዕዘን አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ።
21በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ለአለቃው ይሆናል፤ በመባው በሃያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምዕራቡ ድንበር፥ እንደ ዕጣ ክፍሎች ሁሉ መጠን፥ ለአለቃው ይሆናል፤ የተቀደሰውም መባና ቤተ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል። 22የሌዋውያንም ርስት የከተማይቱም ይዞታ ለአለቃው በሆነው መካከል ይሆናል፤ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበር መካከል የአለቃ ዕጣ ክፍል ይሆናል።
23ለቀሩትም ነገዶች እንዲህ ይሆናል፤ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለብንያም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 24ከብንያምም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለስምዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 25ከስምዖንም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሳኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 26ከይሳኮርም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለዛብሎን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 27ከዛብሎንም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለጋድ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 28ከጋድ ድንበር ቀጥሎ በደቡብ በኩል ድንበሩ ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል። 29ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታካፍሉአት ምድር ይህች ናት፥ የእያንዳንዱም ዕጣ እንደዚህ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
30 #
ራእ. 21፥12፤13። የከተማይቱ መውጫዎች እነዚህ ናቸው። በሰሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው። 31የከተማይቱ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይጠራሉ፤ በሰሜን በኩል ሦስት በሮች አሉ፥ አንዱ የሮቤል በር፥ አንዱ የይሁዳ በር፥ አንዱ ደግሞ የሌዊ በር ነው። 32በምሥራቅ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው፥ ሦስት በሮችም አሉ፤ አንዱ የዮሴፍ በር፥ አንዱ የብንያም በር፥ አንዱ ደግሞ የዳን በር ነው። 33በደቡብ በኩል ልኩ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው፥ ሦስት በሮችም አሉ፤ አንዱ የስምዖን በር፥ አንዱ የይሳኮር በር አንዱ ደግሞ የዛብሎን በር ነው። 34በምዕራቡም በኩል ልኩ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው፥ ሦስት በሮችም አሉ፤ አንዱ የጋድ በር፥ አንዱ የአሴር በር፥ አንዱ ደግሞ የንፍታሌም በር ነው። 35ዙሪያዋ ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማይቱ ስም፦ “ጌታ በዚያ አለ” ተብሎ ይጠራል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 48: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ