ትንቢተ ሕዝቅኤል መግቢያ

መግቢያ
ነቢዩ ሕዝቅኤል ኢየሩሳሌም ከመፍረስዋ በፊትና ከመፍረስዋም በኋላ፥ (በአምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ዓመት) ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በፊት፥ በስደት በባቢሎን ይኖር ነበር። የእርሱ የትንቢት ቃል የተነገረው በባቢሎን በስደት ለሚገኙትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ሕዝብ ነበር። ትንቢተ ሕዝቅኤል አራት ዐበይት ነጥቦች አሉት።
1. የእግዚአብሔር ፍርድ በሕዝቡ ላይ ሊመጣ መቃረቡንና የኢየሩሳሌም መያዝና መፍረስ የደረሰ ስለ መሆኑ፤
2. እግዚአብሔር ሕዝቡን የጨቈኑትንና ያሳሳቱትን ልዩ ልዩ መንግሥታት የሚቀጣ ስለ መሆኑ፤
3. ከኢየሩሳሌም መውደቅ በኋላ እስራኤልን ለማጽናናት መልእክት ስለ መሰጠቱና ወደፊትም መልካም ዕድል እንደሚገጥማት ስለ መነገሩን፤
4. ቤተ መቅደሱና የእስራኤል መንግሥት ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንደሚመለስ ሕዝቅኤል ሥዕላዊ መግለጫ ስለ ማቅረቡ ናቸው።
ሕዝቅኤል ታላቅ እምነትና አርቆ አስተዋይነት ነበረው። የወደፊቱን ሁኔታ በራእይ መልክ ተመልክቶታል፤ መልእክቱ በአብዛኛው የተላለፉት በምሳሌያዊ ንግግርና ድርጊት ነበር። ሕዝቅኤል ውስጣዊ የሆነ የልብና የመንፈስ መታደስ አስፈላጊ መሆኑንና እያንዳንዱ ሰው ስለ ራሱ ኃጢአት ተጠያቂ መሆኑን በአንክሮ አመልክቷል። ከዚሁም ጋር የሕዝቡ ሕይወት ስለ መታደሱ ያለውን ተስፋ ገልጦአል። ሕዝቅኤል ካህንም ነቢይም እንደመሆኑ መጠን ስለ ቤተ መቅደሱና ስለ ቅድስና አስፈላጊነት የተለየ ቀናኢነት ነበረው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ሕዝቅኤል የእግዚአብሔርን ክብር ማየቱና የእርሱም ነቢይ እንዲሆን መመረጡ (1፥1—3፥27)
ይሁዳና ኢየሩሳሌም የሚደመሰሱ መሆናቸውን ሕዝቅኤል በምሳሌ ማስረዳቱ (4፥1—5፥17)
ጥፋት መቃረቡ (6፥1—7፥27)
የእግዚአብሔር ክብር ኃጢአተኛይቱን ኢየሩሳሌምን መተዉ (8፥1—11፥25)
የይሁዳና የኢየሩሳሌም ውድቀት (12፥1—24፥27)
በሌሎች አገሮች ላይ የተላለፈ ፍርድ (25፥1—32፥32)
ሕዝቡ ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ሕዝቅኤል ማስጠንቀቅ የሚገባው መሆኑ (33፥1-20)
የኢየሩሳሌም ውድቀት ዜና (33፥21-33)
ሕዝቡን እንደሚመልስና ይሁዳን እንደሚያድን እግዚአብሔር ተስፋ መስጠቱ (34፥1—37፥28)
ጎግ ተሸንፎ እስራኤል እንደምትመለስ (38፥1—39፥29)
ሕዝቅኤል ወደፊት ስለሚሠራው ቤተ መቅደስ ያየው ራእይ (40፥1—46፥24)
ከቤተ መቅደሱ ሥር ስለሚፈልቀው ውሃ (47፥1-12)
ለእስራኤላውያን የሚመለሰላቸው የጥንት ርስታቸው ድንበርና ለየነገዱ የተደረገ ክፍፍል (47፥13—48፥35)
ምዕራፍ

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ