ወደ ገላትያ ሰዎች 4
4
የእግዚአብሔር ልጆች ስለመሆናችን
1ይህንን እላለሁ፤ ወራሹ በሕፃንነት ዘመኑ ሁሉ፥ ምንም እንኳ የሁሉ ጌታ ቢሆንም ከባርያ አይለይም፤ 2ነገር ግን አባቱ እስከወሰነለት ጊዜ ድረስ በጠባቂዎችና በመጋቢዎች ሥር ነው። 3እኛም ደግሞ ሕፃናት በነበርንበት ጊዜ ከዓለም የመጀመሪያ ትምህርቶች ሥር ተገዝተን ነበር፤ 4የዘመኑ ሙላት በመጣ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ፤ 5#ሮሜ 8፥15-17።ይህም ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት፥ እኛም ልጅነትን እንድናገኝ ነው። 6#3፥26፤ ሮሜ 8፥15።ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር “አባ አባት” ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። 7ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባርያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በእግዚአብሔር በኩል ወራሽ ነህ።
ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች እንደ ተጨነቀ
8ነገር ግን ቀድሞ እግዚአብሔርን ሳታውቁ፥ በተፈጥሮአቸው አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ነበር፤ 9አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችሁ ይልቁንም በእግዚአብሔር ታውቃችሁ፥ እንደገና ወደ ደካማና ወደ ተናቀ የመጀመሪያ ትምህርቶች ዳግም ልትገዙላቸው ፈልጋችሁ እንዴት ትመለሳላችሁ? 10ቀኖችን፥ ወሮችን፥ ዘመናትንና ዓመታትን በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ። 11ምናልባት ስለ እናንተ በከንቱ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
12ወንድሞች ሆይ! እኔ እንደ እናንተ እንደሆንኩ “እንደ እኔ ሁኑ” ብዬ እለምናችኋለሁ። እናንተ አንዳችም አልበደላችሁኝም። 13ቀድሞ በሥጋ ድካም ወንጌልን እንደሰበክሁላችሁ ታውቃላችሁ፤ 14በሥጋዬ ፈተና የሆነባችሁን ነገር አልናቃችሁትም፥ አልተጸየፋችሁትምም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ፥ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ። 15እንግዲህ መባረካችሁ የት አለ? ቢቻል ኖሮ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ እመሰክርላችኋለሁ። 16ስለዚህ እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላታችሁ ሆንሁን? 17ይቀኑባችኋል፥ ለመልካም ግን አይደለም፤ ነገር ግን እናንተ በእነርሱ ላይ እንድትቀኑ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ። 18ሁልጊዜ መልካም ለሆነ ነገር ሁሉ ብትቀኑ መልካም ነው፤ ነገር ግን እኔ ከእናንተ ጋር ባለሁበት ጊዜ ብቻ አይደለም። 19ልጆቼ ሆይ! ክርስቶስ በእናንተ እስኪቀረጽ ድረስ ስለ እናንተ እንደገና ምጥ ይዞኛል። 20አሁን ከእናንተ ጋር ተገኝቼ አነጋገሬን ብለውጥ በወደድሁ ነበር፥ በእናንተ ምክንያት ግራ ገብቶኛልና።
የአጋርና የሣራ ምሳሌነት
21እናንተ ከሕግ በታች ለመኖር የምትፈልጉ፥ እስኪ ንገሩኝ፥ ሕጉን አልሰማችሁትምን? 22#ዘፍ. 16፥15፤ ዘፍ. 21፥2።አብርሃም አንዱን ከባርያይቱ ሌላኛውንም ከነጻይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተጽፎአል። 23ነገር ግን የባርያይቱ ልጅ በሥጋ ልማድ ተወለደ፥ የነጻይቱ ልጅ ግን በተስፋው ቃል መሠረት ተወለደ። 24እነዚህም ምሳሌዎች ናቸው፤ እነዚህም ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና፥ አንደኛዋ ከሲና ተራራ ልጆችን ለባርነት ትወልዳለች፥ እርሷም አጋር ናት። 25ስለዚህ አጋር በዓረብ አገር ያለችው ሲና ተራራ ናት፤ አሁን ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና። 26#ዕብ. 12፥22፤ ራእ. 21፥2።ከላይ የሆነችው ኢየሩሳሌም ግን ነጻ ናት፤ እርሷም እናታችን ናት። 27#ኢሳ. 54፥1።“አንቺ የማትወልጅ መካን! ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ! እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና” ተብሎ ተጽፎአልና። 28ወንድሞች ሆይ! እናንተም እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ናችሁ። 29#ዘፍ. 21፥9።ነገር ግን በዚያን ጊዜ በሥጋ የተወለደው በመንፈስ የተወለደውን እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው። 30#ዘፍ. 21፥10።ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? “የባርያይቱ ልጅ ከነጻይቱ ልጅ ጋር እንዳይወርስ፥ ባርያይቱን ከልጇ ጋር አስወጣት” 31ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! የነጻይቱ ልጆች ነን እንጂ የባርያይቱ አይደለንም።
Currently Selected:
ወደ ገላትያ ሰዎች 4: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ