የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 23

23
የሣራ መሞትና የአብርሃም የመቃብር ቦታ መግዛት
1የሣራም ዕድሜ መቶ ኻያ ሰባት ዓመት ሆነ፥ እነዚህ ሣራ የኖረችባቸው ዓመታት ነበሩ። 2በከነዓንም ምድር ባለችው ቂርያት-አርባዕ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ። 3ከዚያም አብርሃም የሚስቱ አስከሬን ካለበት ስፍራ ተነሥቶ ወደ ሒታውያን ሄደና እንዲህ አላቸው፦ 4#ዕብ. 11፥9፤13፤ የሐዋ. 7፥16።“እኔ በመካከላችሁ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ፥ በእናንተ ዘንድ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፥ ሬሳዬንም ከፊቴ አርቄ ልቅበር።” 5ሒታውያንም እንዲህ ብለው ለአብርሃም መለሱለት፥ 6“ጌታዬ ሆይ፥ እስቲ ስማን፤ አንተ በመካከላችን እንደ ታላቅ መስፍን ነህ፤ ከመቃብሮቻችን ጥሩውን መርጠህ ሬሳህን እዚያ ቅበር፤ ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም።” 7አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ በሒታውያን ፊት እጅ ነሣ። 8እንዲህም አላቸው፦ “ሬሳዬን ከፊቴ አርቄ እንድቀብር ከወደዳችሁስ ስሙኝ፥ ከሰዓር ልጅ ከኤፍሮንም ለምኑልኝ፥ 9በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን ይስጠኝ፥ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንዲሰጠኝ አድርጉልኝ።” 10ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፥ የኬጢ ሰው ኤፍሮንም የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 11“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ስማኝ፥ እርሻውን በክልሉ ውስጥ ካለው ዋሻ ጋር ሰጥቼሃለሁ፤ ሙታንህን እንድትቀብርበት በወገኖቼ በሒታውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ።” 12አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት እጅ ነሣ፤ 13የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ፈቃድህ ከሆነ፥ አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ፥ አንተም ከእኔ ተቀበለኝና የሚስቴን አስክሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው። 14ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 15“ጌታዬ ሆይ፥ እኔን ስማኝ፥ የአራት መቶ ሰቅል ዋጋ መሬት በእኔና በአንተ መካከል ምንድነው? እንግዲህ ሬሳህን ቅበር።” 16አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። 17በዚህ ዓይነት ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ የተባለው የዔፍሮን ቦታ የአብርሃም ርስት ሆነ፤ ይህም ቦታ እርሻውን፥ በውስጡ ያለውን ዋሻና በእርሻው ክልል ውስጥ ያለውን ዛፍ ሁሉን፤ 18በሒታውያን ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ መሆኑ አረጋገጡለት። 19ከዚህም በኋላ ኬብሮን በምትባል፥ ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ፥ በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው፥ ዋሻ ውስጥ አብርሃም ሚስቱን ሣራን ቀበረ። 20እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በሒታውያን ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ