ኦሪት ዘፍጥረት 46
46
ያዕቆብ ወደ ግብጽ ሄደ
1እስራኤልም ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፥ ወደ ቤርሳቤህ ደረሰ፥ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ። 2እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ጠራው። እርሱም፦ “እነሆኝ” አለ። 3እሱም አለው፦ “የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፥ ወደ ግብጽ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና። 4እኔ ወደ ግብጽ አብሬህ እወርዳለሁ፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፥ የዮሴፍም እጅ ዓይንህን ይሸፍናል።”#46፥4 በምትሞትበትም ጊዜ ዮሴፍ ይቀብርሃል 5ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ተነሣ፥ የእስራኤልም ልጆች ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በሰደዳቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃናቶቻቸውን ሴቶቻቸውንም ወሰዱ። 6#የሐዋ. 7፥15።እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ መጡ፥ 7ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ ወሰደ።
የያዕቆብ ቤተሰብ
8ወደ ግብጽም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፥ ያዕቆብና ልጆቹ፥ የያዕቆብ በኩር ሮቤል። 9የሮቤልም ልጆች፥ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ካርሚ። 10የስሞዖን ልጆች፥ ይሙኤል፥ ያሚን፥ አሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል። 11የሌዊም ልጆች፥ ጌድሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። 12የይሁዳም ልጆች፥ ዔር፥ ኦውናን፥ ሴላ፥ ፋሬስ፥ ዛራሕ፥ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ፥ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል። 13የይሳኮር ልጆች፥ ቶላዕ፥ ፉዋ፥ ዮብ፥ ሺምሮን። 14የዛብሎንም ልጆች፥ ሴሬድ፥ ኤሎን፥ ያሕልኤል። 15ልያ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና፥ ሴቲቱ ልጇ ዲና እነዚህ ናቸው፥ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ናቸው። 16የጋድም ልጆች፥ ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ ኤጽቦን፥ ዔሪ፥ አሮዲ፥ አርኤሊ። 17የአሴር ልጆች፦ ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ናቸው። እኅታቸው ሤራሕ ትባላለች። የበሪዓ ልጆች ደግሞ ሔቤርና ማልኪኤል ናቸው። 18እነዚህ ዐሥራ ስድስቱ ላባ ለልጁ ለልያ በሞግዚትነት ከሰጣት ከዚልፋ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። 19ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ዮሴፍና ብንያም ናቸው። 20#ዘፍ. 41፥50-52።የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ናቸው፤ እነርሱም ዮሴፍ በግብጽ ምድር ከኦን ከተማ ካህን ከጶጢፌራ ሴት ልጅ ከአስናት የወለዳቸው ናቸው። 21የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው። 22እነዚህ ዐሥራ አራቱ ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። 23የዳን ልጅ ሑሺም ነው። 24የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጼርና ሺሌም ናቸው። 25እነዚህ ሰባቱ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። 26ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የሄዱት የያዕቆብ ቤተሰቦች ሥልሳ ስድስት ናቸው፤ ይህም የልጆቹን ሚስቶች ቊጥር ሳይጨምር ነው። 27#የሐዋ. 7፥14።ለዮሴፍ በግብጽ ከተወለዱት ከሁለቱ ወንዶች ልጆች ጋር፥ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ቊጥር በአጠቃላይ ሰባ ነበር።
ዮሴፍ ተቀበላቸው
28በጌሴም ምድር እንዲቀበለው ያዕቆብ ይሁዳን ወደ ዮሴፍ አስቀድሞ ላከው፤ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ። 29ዮሴፍም ሠረገላውን አዘጋጀ፥ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ፥ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ፥ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ። 30እስራኤልም ዮሴፍን፥ “አንተ በሕይወት መኖርህን ፊትህን አይቼ አረጋግጫለሁና፥ አሁን ልሙት አለው።” 31ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እኔ መጥቼ ለፈርዖን፦ ‘እንግዲህ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤት ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፥ 32እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፥ እንስሳ ያረቡ ነበርና፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ፥’ ብዬ እነግረዋለሁ። 33ፈርዖንም ቢጠራችሁ፦ ‘ሥራችሁስ ምንድነው?’ ቢላችሁ፥ 34በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 46: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ