ትንቢተ ሆሴዕ 1
1
1 #
2ነገ. 15፥1-7፤ 2ዜ.መ. 26፥1-23፤ 2ነገ. 15፥32-38፤ 2ዜ.መ. 27፥1-8፤ 2ነገ. 16፥1-20፤ 2ዜ.መ. 28፥1-27፤ 2ነገ. 18፥1—20፥21፤ 2ዜ.መ. 29፥1—32፥33፤ 2ነገ. 14፥23-29። በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።
የነቢዩ ሆሴዕ ቤተሰብ
2ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው። 3እርሱም ሄዶ የዴቤላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደችለት። 4#2ነገ. 10፥11።ጌታም እንዲህ አለው፦ “ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤ 5በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ።” 6ዳግመኛም ፀነሰች ሴት ልጅም ወለደች። ጌታም እንዲህ አለው፦ “የእስራኤልን ቤት ፈጽሞ ይቅር እንድላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ርኅራኄ የለኝምና ስምዋን ሎሩሃማ#1፥6 ሎሩሃማ “ምሕረት አልባ” ማለት ነው። ብለህ ጥራት፤ 7ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፤ እነርሱንም በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በጌታ አድናቸዋለሁ።” 8ሎሩሃማንም ጡት ባስጣለች ጊዜ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። 9ጌታም፦ “ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና ስሙን ሎዓሚ#1፥9 ሎዓማ “ሕዝቤ ያልሆነ” ማለት ነው። ብለህ ጥራው፥” አለው።
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 1: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ