ትንቢተ ኢሳይያስ 22
22
1ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ራእይ። እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰገነት መውጣታችሁ ምን ማለት ነው? 2አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም? 3አለቆችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፥ ያለ ቀስትም ተማረኩ፤ እርቀው ቢሸሹም አንቺ ጋር የተገኙት ሁሉ በአንድነት ታሰሩ። 4ስለዚህ፦ “ከእኔ እራቁ፤ መራራ ልቅሶ ላልቅስበት፤ ስለ ሕዝቤ ጥፋት ልታጽናኑኝ አትድከሙ” አልኩ። 5ከሠራዊት ከጌታ በራእይ ሸለቆ ውስጥ የድንጋጤና የመረገጥ፥ ግራ የመጋባት፥ የቅጥር መፍረስና ወደ ተራራ ለእርዳታ የሚጮኽበት ቀን ሆኖአል። 6ኤላምም ከሰረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፥ ቂርም ጋሻውን አነገበ። 7ምርጦቹም ሸለቆችሽ ሠረገሎች ሞሉባቸው፤ ፈረሰኞችም በሮች ላይ ቆመዋል። 8የይሁዳንም መጋረጃ ገልጧል። በዚያም ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን የጦር ዕቃ ተመለከትህ፤ 9የዳዊትም ከተማ ፍራሾች እንደበዙ አይታችኋል፥ የታችኛውንም ኩሬ ውኃ አጠራቅማችኋል። 10የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጠራችሁ፥ ቅጥሩንም ለመጠገን ቤቶችን አፈረሳችሁ። 11በአሮጌው ኩሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፥ ቀድሞ አቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም። 12በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ፥ ጠጉራችሁን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራችሁ። 13#1ቆሮ. 15፥32።ነገር ግን እናንተ፦ “ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣም” በማለት እነሆም፥ በሐሤትና በደስታ በሬንና በጉንም ስታርዱ፥ ሥጋንም ስትበሉ፥ የወይን ጠጅንም ስትጠጡ ነበር። 14ይህም ነገር የሠራዊት ጌታ ይህንን በጆሮዬ ነገረኝ፤ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 15የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በቤቱ ውስጥ ወደ ተሾመው ወደዚህ መጋቢ ወደ ሳምናስ ሂድ እንዲህም በለው፦ 16መቃብር በዚህ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ሥፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖሪያ ያሳነጽክ በዚህ ስፍራ ምን መብት አለህ? በዚህስ ለአንተ ወገን የሆነ ማን አለ? 17እነሆ ወዳጄ፥ ጌታ በኃይል ወርውሮ ይጥልሃል፥ አጥብቆም ሊጨብጥህ ነው፤ 18ጠቅልሎም ያንከባልልሃል፥ ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይወረውርሃል፤ አቤት፥ አንተ የጌታህ ቤት እፍረት! በዚያም ትሞታለህ፥ በዚያም የክብርህ ሠረገላዎች ይቀራሉ። 19ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ ከሹመትህም ትሻራለህ። 20በዚያም ቀን አገልጋዬን የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፥ 21መጎናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፥ በመታጠቅያህም አስታጥቀዋለሁ፥ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል። 22#ራእ. 3፥7።የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። 23በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፥ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል። 24የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፥ እያንዳንዷን ትንንሽ ዕቃ፥ ከሲኒ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል። 25በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለው ችንካር ይወልቃል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ይጠፋል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 22: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ