ትንቢተ ኢሳይያስ 33
33
1አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ አንተም ሳትካድ ክህደትን የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትን በተውክ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መካድን በተውክ ጊዜ ትካዳለህ። 2አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ማረን፤ አንተን እንጠባበቃለን፤ በየእለቱ ክንዳችን፥ በመከራም ጊዜ መድኅኒት ሁነን። 3ከፍጅት ድምፅ ሕዝቦች ሸሹ፤ በመነሣትህም መንግሥታት ተበተኑ። 4አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰብስባለች፤ ኩብኩባም እንደሚዘል ሰዎች ይዘልሉበታል። 5ጌታም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት። 6የዘመንህም ጸጥታ የመድኃኒት፥ የጥበብና የእውቀት ብዛት ይሆናል፤ ጌታን መፍራት ሀብቱ ነው። 7እነሆ፥ ኃይለኞቻቸው በሜዳ ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞች መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ። 8አውራ ጎዳናዎች ባድማ ሆኑ፥ መንገዶችም የሚያልፍባቸው ጠፋ፤ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ ከተሞችንም ናቀ፥ ሰውንም አልተመለከተም። 9ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ። 10“አሁን እነሣለሁ” ይላል ጌታ፥ “አሁን እከበራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ። 11ገለባን ትጸንሳላችሁ፥ ዕብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት። 12አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።” 13እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፤ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እውቁ። 14በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?” 15በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው። 16እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የማታቋርጥ ትሆናለች።
የከበረ ንጉሥ ምድር
17ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ይመለከታሉ። 18ልብህም፦ “ጸሐፊ ወዴት አለ? መዛኝስ ወዴት አለ? ግንቦቹንስ የቈጠረ ወዴት አለ?” ብሎ የሚያስፈራ ነገር ያስባል። 19ከእንግዲህ ወዲህ ጨካኝን ሕዝብ፥ ቋንቋው ለማስተዋል የማይገባ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ አታይም። 20የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ የማይወገድ ድንኳን፥ ካስማውም ለዘለዓለም የማይነቀል፥ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ። 21ጌታ ግን በእነዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ በግርማ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፤ ታላላቅ መርከቦች አያልፉባትም። 22ጌታ ፈራጃችን ነው፥ ጌታ ሕግን ሰጪያችን ነው፥ ጌታ ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል። 23ገመዶችህ ላልተዋል፥ ችካላቸውንም አልጸናም፥ ሸራውንም መወጠር አልቻሉም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ሀብት ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ከክፍፍሉ ይደርሳቸዋል። 24በዚያም የሚኖር ማንም፦ “ታምሜአለሁ” አይልም፤ በእርሷም ለሚኖሩ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 33: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ