ትንቢተ ኢሳይያስ 36
36
የሰናክሬም ወረራ
1በንጉሡ በሕዝቅያስ በዓሥራ አራተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ተመሸጉት ወደ ይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወረራ በመፈጸም ያዛቸው። 2ከዚያ የአሦር ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። እርሱም በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ላይ ባለችው በላይኛይቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ በቆመ ጊዜ፥ 3የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኤልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊውም ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአስ፥ ወደ እርሱ መጡ። 4ራፋስቂስም እንዲህ አላቸው፦ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የምትተማመንበት መተማመኛ ምንድነው? 5ባዶ ቃል የጦር ስልትና ኃይል የሚሆንህ ይመስልህል? አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው? 6#ሕዝ. 29፥6፤7።እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ የሸንበቆ በትር በግብጽ ተማምነሀል፤ ሰው ተማምኖ ቢመረኰዘው እጁን ወግቶ ያቈስለዋል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርኦን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው። 7አንተም፦ ‘በአምላካችን በጌታ እንታመናለን’ ብትለኝ፥ ‘በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ’ ብሎ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ሕዝቅያስ ያስፈረሰው እርሱ አይደለምን? 8እንግዲህ አሁን ናና፥ ከአለቃዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተደራደርና፥ የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ካገኘህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ። 9ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሰኞች በግብጽ ስትታመን፥ ከአለቃዬ ባርያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ለመቃወም እንዴት ይቻልሃል? 10አሁንም ቢሆን፥ ጌታ፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ እንጂ፥ በውኑ ያለ ጌታ ይህን አገር ለማጥፋት የዘመትኩ ይመስልሃል?”
11ከዚያም ኤልያቄም፥ ሳምናስና ዮአስ ራፋስቂስን፦ “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሚገባን በሶርያ ቋንቋ#36፥11 አራማይክ። ለአገልጋዮችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ መግባቢያ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን” አሉት። 12ራፋስቂስ ግን፦ “አለቃዬ ይህን ቃል እንድናገር ወደ እናንተና ወደ አለቃችሁ ብቻ ልኮኛልን? እንደ እናንተ የራሳቸውን ኩስ ለመብላትና ሽንታቸውንም ለመጠጣት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ጭምር አይደለምን?” አላቸው። 13ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኸ፦ “የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ። 14ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቅያስ ሊያድናችሁ አይችልምና አያታላችሁ፤ 15ሕዝቅያስ፥ ጌታ በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም፥ ብሎ በጌታ እንድትታመኑ አያድርጋችሁ። 16ሕዝቅያስን አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ኑ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጉድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤ 17ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፥ እህልና የወይን ጠጅ፥ እንጀራና ወይን ወዳለባት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ ነው። 18ሕዝቅያስ፥ ጌታ ያድነናል ብሎ እንዳያታልላችሁ ተጠንቀቁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት አገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋል? 19የሐማትና የአልፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታል? 20ጌታ ኢየሩሳሌምን ከእጄ ያድን ዘንድ፥ ከእነዚህ አገሮች ሁሉ አማልክት አገሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?’” 21እነርሱ ግን ዝም አሉ፥ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና “አንዳችም አልመለሱለትም”። 22የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊውም ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአስ፥ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 36: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ