መጽሐፈ መሳፍንት 12
12
ዮፍታሔና ኤፍሬማውያን
1 #
መሳ. 8፥1። የኤፍሬም ሰዎች ኃይላቸውን አሰባስበው ወደ ጻፎን በመሻገር ዮፍታሔን፥ “አሞናውያንን ለመውጋት ስትወጣ አብረንህ እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምንድን ነው? ቤትህን በላይህ ላይ እናቃጥለዋለን አሉት።” 2ዮፍታሔም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋር ከፍተኛ ትግል ገጥመን በነበረበት ጊዜ ጠርቼያችሁ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም፤ 3እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ ጌታም ድሉን ሰጠኝ፤ ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?” 4ከዚያም ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ ከኤፍሬም ጋር ተዋጋ። ኤፍሬማውያን ገለዓዳውያንን፥ “እናንተ ገለዓዳውያን ከኤፍሬምና ከምናሴ የከዳችሁ ናችሁ” ይሏቸው ስለ ነበር በብርቱ መቷቸው። 5ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥ 6እስቲ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ታዲያ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ ይዘው እዚያው መሻገርያው ላይ ይገድሉታል፤ በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ።
7 #
መሳ. 10፥2፤ 5፤ 12፥10፤ 12፤ 15፤ 15፥20። ዮፍታሔ በእስራኤል ላይ ለስድስት ዓመት ፈራጅ ሆነ። ገለዓዳዊው ዮፍታሔ ሞተ፤ ከገለዓድም ከተሞች በአንዲቱ ተቀበረ።
ኢብጻን፥ ኤሎም፥ ዔብዶን
8ከዮፍታሔ ቀጥሎ የቤተልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ላይ ፈራጅ ሆነ። 9#መሳ. 8፥30፤ 9፥2፤ 5፤ 10፥4፤ 12፥14።እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ። 10ኢብጻን ሞተ፤ በቤተልሔምም ተቀበረ።
11ከእርሱም በኋላ ዛብሎናዊው ኤሎም በእስራኤል ላይ ዐሥር ዓመት ፈራጅ ሆነ። 12ከዚያም ኤሎም ሞተ፤ በዛብሎን ምድር በኢያሎን ተቀበረ።
13ከኤሎም ቀጥሎ የጲርዓቶናዊው የሂሌል ልጅ ዓብዶን በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 14#መሳ. 9፥2፤ 5፤ 10፥4፤ 12፥9።እርሱም በሰባ አህዮች ላይ የሚቀመጡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፤ በእስራኤልም ላይ ስምንት ዓመት ፈራጅ ሆነ። 15ከዚያም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፤ ኰረብታማ በሆነው በአማሌቃውያን አገር በኤፍሬም ምድር በጲርዓቶን ተቀበረ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ