የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መሳፍንት 17

17
ሚካ ያሠራቸው ጣዖቶች
1ሚካ የተባለ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር ሰው ነበር። 2እናቱን፥ “አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ብር ተሰርቆብሽ፥ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት። ከዚያም እናቱ፥ “ልጄ፤ ጌታ ይባርክህ” አለችው። 3#ዘፀ. 20፥4፤ ዘሌ. 19፥4፤ ዘዳ. 5፥8።አንድ ሺህ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ፥ እናቱ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄን ለጌታ እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። 4ስለዚህ ብሩን ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱም ከላዩ ሁለት መቶ ጥሬ ብር ወስዳ ለብር አንጥረኛ ሰጠች፤ አንጥረኛውም የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት አደረገው፤ ምስሎቹም በሚካ ቤት ተቀመጡ። 5#መሳ. 18፥14፤ 18።ሚካ የተባለው ይህ ሰው የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ አንድ ኤፉድና ተራፊም ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ።#1ሳሙ. 7፥1። 6#መሳ. 18፥1፤ 19፥1፤ 21፥25።በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።
7 # መሳ. 19፥1። በይሁዳ ምድር፥ በይሁዳ ነገድ መካከል በቤተልሔም የሚኖር አንድ ሌዋዊ ወጣት ነበር። 8ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከተማይቱን ለቆ ሄደ። በሚጓዘበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ። 9ሚካም፥ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው። 10#መሳ. 18፥19።ሚካም፥ “እንግዲያውስ አብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው። 11ስለዚህ ሌዋዊው አብሮት ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። 12ሚካም ሌዋዊውን ካህን አድርጎ አስቀመጠው፤ ወጣቱም ካህኑ ሆነ፤ በቤቱም ኖረ። 13ሚካም፤ “አሁን ሌዋዊ ካህን ስላገኘሁ፥ ጌታ በጎ ነገር እንደሚያደርግልኝ አሁን ተረዳሁ” አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ