የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መሳፍንት 3

3
1በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፥ ጌታ ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው። 2ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው። 3#ኢያ. 13፥2-5።እነዚህም አሕዛብ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማትስ መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ። 4እነርሱም ጌታ በሙሴ አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻቸው የሰጣቸውን ትእዛዞች እስራኤላውያን ያከብሩ ወይም አያከብሩ እንደሆነ ለማወቅ ለእስራኤል መፈተኛዎች ነበሩ። 5#ዘፀ. 3፥8፤ 17፤ 23፥23፤ 33፥2፤ 34፥11፤ ዘዳ. 7፥1፤ 20፥17፤ ኢያ. 3፥10፤ 24፥11።ስለዚህ እስራኤላውያን ከከነዓናውያን፥ ከኬጢያውያን፥ ከአሞራውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋር አብረው ኖሩ። 6#ዘፀ. 34፥16፤ ዘዳ. 7፥3፤ ኢያ. 23፥12።እስራኤላውያን የእነዚህን ሴቶች ልጆች አገቡ፤ የራሳቸውንም ሴቶች ልጆች ለእነርሱ ወንዶች ልጆች ዳሩ፤ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ።
ዖትኒኤል
7 # መሳ. 2፥11-14። እስራኤላውያን በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ አምላካቸውን ጌታንም ረሱ፤ በኣልንና አስታሮትን አመለኩ። 8ጌታ በእስራኤላውያን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ስለዚህ ለመስጴጦምያ ንጉሥ ለኩሽን-ሪሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እስራኤላውያንም ለኩሽን-ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት በባርነት ተገዙለት። 9#መሳ. 3፥15፤ 4፥3፤ 6፥6፤ 7፤ 10፥10፤ 1ሳሙ. 12፥8፤ 10።እስራኤላውያን ወደ ጌታ በጮኹ ጊዜ ግን፥ ጌታ የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው።#መሳ. 1፥13። 10#መሳ. 6፥34፤ 11፥29፤ 13፥25፤ 14፥6፤ 19፤ 15፥14፤ 1ሳሙ. 11፥6።የጌታም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ ጌታ የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሽን ሪሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሽን-ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። 11#መሳ. 3፥30፤ 5፥31፤ 8፥28።የቄኔዝ ልጅ ዖትኒኤል እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።
ኤሁድ
12እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን ክፋት በጌታ ፊት በማድረጋቸው፥ ጌታ የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ። 13እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎችበ ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ። 14እስራኤላውያንም ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን ዐሥራ ስምንት ዓመት ተገዘሉት።
15እስራኤላውያን እንደገና ወደ ጌታ ጮኹ፤ ጌታም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ፥ ግራኙን፥ ኤሁድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። 16እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመትተ ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። 17ግብሩንም ወፍራም ለነበረው ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን አቀረበ። 18ኤሁድ ግብሩን ካቀረበ በኋላ፥ ግብር ተሸክመው የመጡትን ሰዎች ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ። 19እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፥ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩትአገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ። 20ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ቀረብ ብሎ፥ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ። 21ኤሁድ ግራ እጁን ሰደድ በማድረግ ሰይፉን ከደበቀበት ከቀኝ ጭኑ መዝዞ በንጉሡ ሆድ ሻጠው። 22እጀታው ሳይቀር ሰይፉ እንዳለ ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ሞራውም ስለቱን ሸፈነው፤ ስለቱም በጀርባው ወጣ፤ ኤሁድ ሰይፉን ስላልነቀለው አንጀቱ ተዘረገፈ። 23ከዚያም በኋላ ኤሁድ በዕልፍኙ መግቢያ ወጣ፤ የዕልፍኙንም በር በንጉሡ ላይ ዘግቶ ቈለፈው።
24ኤሁድ ከሄደ በኋላ፥ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፥ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፥ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ 25እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የእልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቊልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፥ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት።
26የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ኤሁድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታ ይም አመለጠ። 27እዚያም እንደ ደረሰ፥ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በእርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ አብረውት ወረዱ። 28#ዘኍ. 21፥34፤ ዘዳ. 2፥24፤ ኢያ. 2፥24፤ መሳ. 4፥7፤ 14፤ 7፥7፤ 9፤ 15።እርሱም “ጠላታችሁን ሞዓብን ጌታ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ተከተሉኝ” በማለት አዘዛቸው፤ እነርሱም ተከትለውት ወረዱ፤ ከዚያም ከዮርዳኖስ ወደ ሞዓብ የሚያሻግሩትን ስፍራዎች በመያዝ አንድም ሰው እንዳያልፍ ከለከሉ። 29በዚያን ጊዜ ብርቱና ይለኛ የሆኑ ዐሥር ሺህ ሞዓባውያንን ገደሉ፤ አንድም ሰውአላመለጠም። 30#መሳ. 8፥28፤ 11፥23፤ 1ሳሙ. 7፥13።በዚያን ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች።#መሳ. 3፥11፤ 5፥31፤ 8፥28።
ሻምጋር
31 # መሳ. 5፥6። ከኤሁድ በኋላ ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሻምጋር ተነሣ፤ እርሱም እንደዚሁ ደግሞ እስራኤልን አዳነ።#መሳ. 15፥15፤ 2ሳሙ. 23፥8፤ 18።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ