መጽሐፈ መሳፍንት 9
9
የአቤሜሌክ ንግስና
1 #
መሳ. 8፥31። የይሩባኣል ልጅ አቤሜሌክ ወደ እናቱ ወንድሞች ወደ ሴኬም ሄደ። እነርሱንና የእናቱን ጐሣዎች በሙሉ እንዲህ አላቸው፤ 2#2ሳሙ. 5፥1፤ 19፥12፤ 13።“የሴኬምን ነዋሪዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፤ ‘ሰባዎቹ የይሩባኣል ልጆች ቢገዟችሁ ይሻላል ወይስ አንድ ሰው ብቻ?’ የሥጋችሁ ቁራጭ፥ ያጥንታችሁ ፍላጭ መሆኔን ልብ በሉ።” 3የእናቱ ዘመዶች ስለ እርሱ ሆነው እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለሴኬም ነዋሪዎች በሙሉ ነገሩ፤ “እርሱማ ወንድማችን አይደል” ብለዋልና፥ አቤሜሌክንም ለመከተል ልባቸው ወደሱ አዘነበለ። 4እነርሱም በኣልብሪት ቤተ ጣዖት ሰባ ሰቅል ናስ ሰጡት፤ አቤሜሌክም በዚያ ወሮበሎችንና ምናምንቴዎችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከተሉት። 5ከዚያም ዖፍራ ወደሚገኘው ወደ አባቱ ቤት ሄደ፤ ሰባውን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የይሩበኣል የመጨራሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለ ነበር አመለጠ። 6የሴኬምና የቤትሚሎ ነዋሪዎች በሙሉ አቤሜሌክን ለማንገሥ ሴኬም ውስጥ በዐምዱ አጠገብ ካለው የባሉጥ ዛፍ ሥር ተሰበሰቡ።
7ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፥ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምጽን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ የሴኬም ነዋሪዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ፤ 8ከዕለታት አንድ ቀን ዛፎች የሚያነግሡትን ለመቀባት ወጡ፤ ወይራንም፥ “አንተ ንጉሣችን ሁን” አሉት። 9የወይራ ዛፍም፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ እግዚአብሔርና ሰዎች የሚከበሩበትን ዘይቴን መስጠት ልተውን?” አለ። 10ቀጥሎም ዛፎቹ በለስን፥ “መጥተህ ንጉሣችን ሁን” አሉት። 11በለስ ግን፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ እጅግ ጣፋጭና መልካም የሆነውን ፍሬዬን መስጠት ልተውን?” አለ። 12ከዚያም ዛፎቹ የወይን ተክልን፥ “መጥተህ ንጉሣችን ሁን” አሉት። 13የወይን ተክሉም፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ አማልክትንና ሰዎችን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጄን መስጠት ልተውን?” አለ። 14በመጨረሻም ዛፎቹ በሙሉ የእሾኽ ቊጥቋጦን፥ “መጥተህ ንጉሣችን ሁን” አሉት። 15#2ነገ. 14፥9።የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።
16“እንግዲህ አቤሜሌክን ስታነግሡት በቅንነትና በእውነት አድርጋችሁት ከሆነ፥ ይሩበኣልንና ቤተሰቡን በበጎ ዐይን ተመልክታችሁ ላደረገው የሚገባውን አይታችሁለት ከሆነ፥ 17አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፥ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን አሰባችሁ ማለት ነው። 18#መሳ. 8፥31።ነገር ግን እናንተ ዛሬ በአባቴ ቤተሰብ ላይ ዐመፃችሁ፤ ሰባ ልጆቹን በአንዲት ድንጋይ ላይ ዐረዳችሁ፤ ዘመዳችሁ ስለ ሆነም አባቴ ከባርያው የወለደውን ልጅ አቤሜሌክን በሴኬም ነዋሪዎች ላይ አነገሣችሁት። 19እንግዲህ ዛሬ በይሩበኣልና በቤተሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና በቅንነት ከሆነ እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው 20ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።” 21ከዚህ በኋላ ኢዮአታም ሸሽቶ አመለጠ፤ ብኤር ወደተባለች ቦታም መጣ፤ ወንድሙንም አቤሜሌክን ፈርቶ ስለ ነበር እዚያው ይኖር ጀመር።
22አቤሜሌክ እስራኤልን ሦስት ዓመት ከገዛ በኋላ፥ 23#1ሳሙ. 16፥14፤ 18፥10፤ 19፥9፤ 1ነገ. 22፥19-23።እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ነዋሪዎች መካከል ክፉ መንፈስ ሰደደ፤ ስለዚህም የሴኬም ሰዎች አቤሜሌክን ከዱት። 24እግዚአብሔር ይህን ያደረገውም፥ በሰባው የይሩበኣል ልጆች ላይ ስለ ተፈጸመው ግፍና ስለ ፈሰሰው ደማቸው፥ ወንድማቸውን አቤሜሌክና ወንድሞቹን እንዲገድል የረዱትን የሴኬም ሰዎች ለመበቀል ነው። 25የሴኬም ነዋሪዎችም አቤሜሌክን ሸምቀው የሚጠባበቁትን ሰዎች መደቡ፤ ሰዎቹም እርሱን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በዚያ የሚያልፈውን ሁሉ ዘረፉ፤ ወሬውም ለአቤሜሌክ ደረሰው።
26በዚህ ጊዜ የአቤድ ልጅ ገዓል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም መጣ፤ የሴኬምም ሰዎች ተማመኑበት። 27ወደ ዕርሻ ወጥተው ወይናቸውን ለቅመው ከጨመቁ በኋላ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፤ በዚያም እየበሉና እየጠጡ አቤሜሌክን ሰደቡ። 28#1ሳሙ. 25፥10።የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩበኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቤሜሌክ እንገዛለን?#ዘፍ. 33፥19፤ 34፥2። 29ምነው ይህን ሕዝብ የማዘው እኔ በሆንሁ ኖሮ፥ አቤሜሌክን አስወግደው ነበር፤ ‘ሠራዊትህን አብዝተህ እስቲ ውጣ! እለው ነበር።’”
30የከተማይቱ ገዥ ዜቡል፥ የአቤድ ልጅ ገዓል ያለውን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ 31ወደ አቤሜልክም መልእክተኞች በምስጢር ልኮ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተው ከተማይቱ እንድትሸፍትብህ አድርገዋል። 32ስለዚህ በሌሊት ሰዎችህን ይዘህ ወጥተህ ሜዳው ላይ ማድፈጥ አለብህ፤ 33ጠዋት ፀሓይ ስትወጣም ወደ ከተማይቱ ገሥግሥ፤ ገዓልና ሰዎቹ ሊገጥሙህ በሚወጡበት ጊዜ እጅህ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርግ።”
34ስለዚህ አቤሜሌክና ሰዎቹ በሙሉ በሌሊት ወጡ፤ በአራት ምድብ ሆነውም በሴኬም አጠገብ አደፈጡ። 35የአቤድ ልጅ ገዓል ከከተማይቱ ወጥቶ በመግቢያው በር ላይ ሲቆም፥ አቤሜሌክና ሰዎቹ ካደፈጡበት ወጡ። 36ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፥ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው። ዜቡልም መልሶ፥ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ ነው” አለው። 37ገዓልም፥ “ተመልከት እንጂ ሕዝብ እኮ ከተራራው ወገብ ላይ እየደረሰ ነው፤ አንዱ ክፍልም በአስማተኞች የባሉጥ ዛፍ በኩል አድርጎ እየመጣ ነው” ብሎ እንደገና ተናገረ። 38ከዚያም ዜቡል፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜልክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልካቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው። 39ገዓል የሴኬምን ሰዎች መርቶ በመውጣት አቤሜሌክን ተዋጋው፤ 40ሆኖም አቤሜሌክ አሳደደው፤ እስከ መግቢያው በር ድረስ ባለው መንገድ ሲሸሹም ብዙ ሰዎች ቈስለው ወደቁ።
41አቤሜሌክ በአሩማ ተቀመጠ፤ ዜቡልም ገዓልንና ወንድሞቹን ከሴኬም አስወጣቸው። 42በማግስቱ የሴኬም ሕዝብ ወደ ዕርሻ ወጡ፤ ይህም ለአቤሜሌክ ተነገረው፤ 43እርሱም ሰዎቹን አስከትሎ ወጣ፤ ከዚያም ሰዎቹን ሦስት ቦታ መድቦ በዕርሻዎቹ ውስጥ አድፍጠው እንዲጠባበቁ አደረገ። አቤሜሌክ የሴኬም ሰዎች ከከተማይቱ መውጣታቸውን እንዳየም ካደፈጠበት ሊወጋቸው ተነሣ። 44ከዚያም አቤሜሌክና አብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማይቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፥ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው። 45#ዘዳ. 29፥23፤ ኤር. 17፥6፤ መዝ. 107፥34።በዚያን ዕለት አቤሜሌክ ቀኑን ሙሉ ከተማይቱን ሲወጋ ውሎ በመጨረሻ ያዛት፤ ሕዝቧን ፈጀ፤ ከተማይቱንም አጠፋ፤ በላይዋም ጨው ዘራባት።
46በሴኬም ግምብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ይህን እንደ ሰሙ፤ በኤልበሪት ቤተ መቅደስ ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገቡ። 47አቤሜሌክም በዚያ መመሸጋቸውን ሲሰማ፥ 48እርሱና ሰዎቹ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፤ አቤሜሌክም መጥረቢያ ወስዶ ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ በትከሻውምላይ አደረገ። የተከተሉትንም ሰዎች፥ “ፍጠኑ፤ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን አድርጉ” ሲል አዘዛቸው። 49ሰዎቹም ሁሉ ቅርንጫፎች ቈርጠው አቤሜሌክን ተከተሉት፤ ቅርንጫፎቹንም ምሽጉ ላይ አስደግፈው በመከመር ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉ በእሳት አቃጠሏቸው። ስለዚህ በሴኬም ምሽግ ውስጥ የነበሩት አንድ ሺህ ያህል ወንዶችና ሴቶች ሞቱ።
50ከዚያም አቤሜሌክ ወደ ቴመስ በመሄድ ከተማይቱን ከቦ ያዛት። 51ሆኖም በከተማይቱ ውስጥ ብርቱ ግንብ ስለ ነበር፥ የከተማይቱ ሕዝብ በሙሉ ወንድ ሴት ሳይባል ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በውስጥ ዘግተው ወደ ግንቡ ጣሪያ ወጡ። 52አቤሜሌክም ተዋግቶ ግንቡን ያዘ፤ ይሁን እንጂ እሳት ለመለኮስ ወደ ግንቡ መግቢያ አጠገብ እንደ ደረሰ፥ 53#2ሳሙ. 11፥21።አንዲት ሴት ከላይ የወፍጮ መጅ በራሱ ላይ ለቀቀችበት፤ ጭንቅላቱንም አፈረሰችው። 54#1ሳሙ. 31፥4፤ 2ሳሙ. 1፥9፤ 1ዜ.መ. 10፥4።ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፥ “‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ። 55እስራኤላውያንም አቤሜሌክ መሞቱን ሲያዩ ወደየቤታቸው ተመለሱ። 56አቤሜሌክ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል በአባቱ ላይ ስላደረሰው በደል እግዚአብሔር የእጁን ከፈለው። 57በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰው፤ የይሩበኣል ልጅ የኢዮአታም ርግማን ደረሰባቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 9: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ