የዮሐንስ ወንጌል 16
16
1“እንዳትሰናከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ። 2ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። 3ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው። 4ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከእናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።
የመንፈስ ቅዱስ ሥራ
5“አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ከእናንተም ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም። 6ነገር ግን ይህን ስለ ነገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል። 7እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። 8እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤ 9ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ 10ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤ 11ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።
12“ገና ብዙ የምነግራችሁ አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። 13#ጥበ. 9፥11።የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። 14እርሱ ያከብረኛል፤ የእኔ ከሆነው ወስዶ ይነግራችኋልና። 15በአብ ዘንድ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህም ‘በእኔ ዘንድ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል’ አልሁ።
ኀዘንና ደስታ
16“ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።” 17ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው “ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤”፥ ደግሞ “ወደ አብ እሄዳለሁና፤ የሚለን ነገር ምንድነው?” ተባባሉ። 18“እንግዲህ ‘ጥቂት’ ሲል ምን ማለቱ ነው? የሚናገረውን አናውቅም” አሉ። 19ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ወደዱ አውቆ እንዲህ አላቸው “‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤’ ስላልሁ፥ እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን? 20እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳለችሁ፤ ሙሾም ታወጣላችሁ፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። 21ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና በደስታዋ ምክንያት መከራዋን ከቶውን አታስበውም። 22እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። 23በዚያን ቀንም ከእኔ ምንም ነገር አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። 24እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ፤ ትቀበሉማላችሁ።”
25ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ በምሳሌ ሳይሆን በግልጥ ለእናንተ የምናገርበት ሰዓት ይመጣል። 26በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እለምናለሁ አልላችሁም፤ 27ምክንያቱም አብ እራሱ ስለሚወዳችሁ ነው፤ ይህም እናንተ ስለ ወደዳችሁኝና ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደመጣሁ ስላመናችሁ ነው። 28ከአብ ዘንድ መጣሁ፤ ወደ ዓለምም መጥቻለሁ፤ ደግሞም ዓለምን እተወዋለሁ፤ ወደ አብም እሄዳለሁ።
29ደቀመዛሙርቱ “እነሆ፥ አሁን በግልጥ ትናገራለህ፤ በምሳሌም መናገር አቆምህ። 30ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ፥ እንዲሁም ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናምናለን፤” አሉት። 31ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “አሁን ታምናላችሁን? 32እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም። 33በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤”
Currently Selected:
የዮሐንስ ወንጌል 16: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ