የዮሐንስ ወንጌል 18
18
ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ እንደሰጠ
(ማቴ. 26፥47-56፤ ማር. 14፥43-50፤ ሉቃ. 22፥47-53)
1ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ። 2ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ብዙ ጊዜ ወደዚያ ስለ ተሰበሰቡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ስፍራውን ያውቅ ነበር። 3ስለዚህ ይሁዳ ወታደሮችን፥ እንዲሁም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ሎሌዎችን ተቀብሎ በችቦና በፋና፥ በጦር መሣርያም ታጅቦ ወደዚያ መጣ። 4ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና “ማንን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። 5“የናዝሬቱን ኢየሱስን” ብለው መለሱለት። እርሱም “እኔ ነኝ” አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር። 6ኢየሱስም “እኔ ነኝ” ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በመሬት ላይ ወደቁ። 7ዳግመኛ “ማንን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስን” አሉት። 8ኢየሱስ መልሶ “እኔ ነኝ፤ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ከሆነ የምትፈልጉት እነዚህን ተዉአቸው፤ ይሂዱ” አለ፤ 9ይህም “ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንዱን እንኳን አላጠፋሁም” ያለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። 10ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ይዞ ስለ ነበር መዘዘውና የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ነበረ። 11#ማቴ. 26፥39፤ ማር. 14፥36፤ ሉቃ. 22፥42።ኢየሱስም ጴጥሮስን “ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው፤ አብ የሰጠኝን ጽዋ ላልጠጣ ነውን?” አለው።
የኢየሱስ ወደ ሊቀ ካህናቱ መወሰድ
(ማቴ. 26፥57-58፤ ማር. 14፥53-54፤ ሉቃ. 22፥54)
12እንግዲህ ወታደሮቹና አዛዣቸው፥ የአይሁድም ሎሌዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፤ 13አስቀድመውም ወደ ሐና ወሰዱት፤ በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ለነበረው ለቀያፋ አማቱ ነበርና። 14#ዮሐ. 11፥49፤50።ቀያፋም “ስለ ሕዝቡ ሲባል አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል” ሲል አይሁድን የመከራቸው ነበረ።
ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደ ካደ
(ማቴ. 26፥69-70፤ ማር. 14፥66-68፤ ሉቃ. 22፥55-57)
15ስምዖን ጴጥሮስና ሌላው ደቀመዝሙር ኢየሱስን ተከተሉ። ያም ደቀመዝሙር በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀ ነበረ፤ ወደ ሊቀ ካህናቱም ግቢ ከኢየሱስ ጋር ገባ፤ 16ጴጥሮስ ግን በውጭ በበሩ ቆሞ ነበር። በሊቀ ካህናቱም ዘንድ የታወቀው ሌላው ደቀመዝሙር ወጣ፤ ለበረኛይቱም ነግሮ ጴጥሮስን አስገባው። 17በር ጠባቂ አገልጋይቱም ጴጥሮስን “አንተም ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ አይደለህምን?” አለችው። እርሱ “አይደለሁም” አለ። 18ይበርድ ነበረና አገልጋዮችና ሎሌዎች የከሰል እሳት አንድደው ቆመው ይሞቁ ነበር፤ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበር።
ከሊቀ ካህናቱ ለኢየሱስ የቀረበ ጥያቄ
(ማቴ. 26፥59-66፤ ማር. 14፥55-64፤ ሉቃ. 22፥66-71)
19ሊቀ ካህናቱም ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው። 20ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም። 21ስለምን እኔን ትጠይቀኛለህ? ስናገር የሰሙኝን ጠይቅ፤ እነሆ፥ እነርሱ እኔ የተናገርሁትን ያውቃሉ፤” አለው። 22ይህንን ባለ ጊዜ በዚያ ቆመው ከነበሩት ሎሌዎች አንዱ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን?” ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው። 23ኢየሱስም መልሶ “ክፉ ተናግሬ እንደሆነ ስለ ክፉ መስክርብኝ፤ መልካም ተናግሬ እንደሆን ግን ስለምን ትመታኛለህ?” አለው። 24ሐናም እንደታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።
ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደገና መካዱ
(ማቴ. 26፥71-75፤ ማር. 14፥69-72፤ ሉቃ. 22፥58-62)
25ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። “አንተስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም “አይደለሁም፤” ብሎ ካደ። 26ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች መካከል አንዱ፥ ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ፥ “በአትክልቱ ስፍራ ከእርሱ ጋር አይቼህ አልነበረምን?” አለው። 27ጴጥሮስም በድጋሚ ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።
ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት እንደ ቆመ
(ማቴ. 27፥1-2፤11-14፤ ማር. 15፥1-5፤ ሉቃ. 23፥1-5)
28ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ማለዳም ነበረ፤ እነርሱም እንዳይረክሱ፥ ይልቁንም የፋሲካን በግ እንዲበሉ በማለት ወደ ገዢው ግቢ አልገቡም። 29ስለዚህም ጲላጦስ ወደ ውጭ፥ ወደ እነርሱ ወጥቶ “በዚህ ሰው ላይ የምታቀርቡት ምን ዓይነት ክስ ነው አላቸው?” አላቸው። 30እነርሱም መልሰው “ይህ ሰው ክፉ አድራጊ ባይሆን ለአንተ አሳልፈን ባልሰጠነውም ነበር” አሉት። 31ጲላጦስም “እናንተ ወስዳችሁ በሕጋችሁ ፍረዱበት” አላቸው። አይሁድም “እኛስ ማንንም ለመግደል አልተፈቀደልንም፤” አሉት፤ 32#ዮሐ. 3፥14፤ 12፥32።ይህም ኢየሱስ በምን ዓይነት ሞት እንደሚሞት ሲያመለክት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነብር።
33ጲላጦስም እንደገና ወደ ገዢው ግቢ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው። 34ኢየሱስም መልሶ “አንተ ይህን የምትለው ከራስህ ነውን? ወይስ ሌሎች ስለ እኔ ነገሩህ?” አለው። 35ጲላጦስ መልሶ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው። 36ኢየሱስም መልሶ “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ ነገር ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም” አለው። 37ጲላጦስም “እንግዲያውስ ንጉሥ ነህን?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ተወልጃለሁ፤ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል” አለው። 38ጲላጦስ “እውነት ምንድነው?” አለው።
ይህንንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጣና “እኔስ አንዲት በደል እንኳን አላገኘሁበትም። 39ነገር ግን በፋሲካ አንድ ሰው እንድፈታላችሁ ልማድ ሆኖአል፤ የአይሁድን ንጉሥ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁን?” አላቸው። 40ሁሉም በድጋሚ “በርባንን እንጂ ይህን ሰው አይደለም” እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ።
Currently Selected:
የዮሐንስ ወንጌል 18: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ