የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዮናስ 3

3
የነነዌ መመለስ
1የጌታም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዮናስ መጣ፥ እንዲህ አለው፦ 2“ተነሥ፥ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ እኔ የምነግርህን መልዕክት አውጅ።” 3ዮናስም ተነሣና ጌታ እንደ ተናገረው ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች፥ ለማቋረጥም ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር። 4#ማቴ. 12፥41፤ ሉቃ. 11፥32።ዮናስ ወደ ከተማይቱ መግባት ጀመረ፥ የአንድ ቀን መንገድ ያህል እንደ ገባ “አሁንም ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ጮኸ።
5የነነዌም ሰዎች በእግዚአብሔር አመኑ፤ ጾምም አወጁ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። 6ይህ ወሬ ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፥ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፥ ማቅ ለበሶ በአመድም ላይ ተቀመጠ። 7በነነዌ ሁሉ ይህንን አዋጅ አስነገረ፦ በንጉሡና በመኳንንቱ ትእዛዝ መሠረት፥ ሰውም ሆነ እንስሳ፥ ከብትም ሆነ በግ አንዳች አይቅመሱ፤ አይሰማሩ፥ ውኃም አይጠጡ፥ 8ሰውም ሆነ እንስሳ በማቅ ይሸፈኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎች ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በመዳፋቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። 9እኛ እንዳንጠፋ፥ እግዚአብሔር ራርቶ ከሚነደው ቁጣው ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል? 10እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፥ እግዚአብሔርም ራርቶ አደርግባችኋለሁ ብሎ የተናገረውን ክፉ ነገር አላደረገውም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ