የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዮናስ መግቢያ

መግቢያ
ትንቢተ ዮናስ፥ የእግዚአብሔርን ተልእኮ በሸሸ በአንድ ነቢይ ላይ የሚደርሰውን ችግር የሚገልጥ መጽሐፍ በመሆኑ ከሌሎች የትንቢት መጻሕፍት የተለየ መልክ አለው። እግዚአብሔር ዮናስን “የእስራኤል ብርቱ ጠላትና የታላቁ የአሦር መንግሥት ዋና ከተማ ወደነበረችው ወደ ነነዌ ሂድ!” በማለት አዘዘው፤ ዮናስ ግን “እግዚአብሔር ከተማይቱን ለማጥፋት የሰጠውን ብርቱ ማስጠንቀቂያ በሥራ ላይ ላያውለው ይችላል” ብሎ ስላሰበ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ይዞ ወደ ነነዌ መሄድ አልፈለገም፤ ብዙ ውጣ ውረድ ካሳለፍ በኋላ ደስ ሳይለው ታዘዘ፤ “ነነዌ ትጠፋለች” ብሎ ተነበየ። ንጉሡ፥ ሕዝቡና እንስሳት የእግዚአብሔርን ምሕረት ለማግኘት ብለው ማቅ ለብሰው መጾም ጀመሩ። ንሥሐ በመግባታቸው ዮናስ የፈራው ነገር ተከሠተ፤ ነነዌም ከጥፋት ዳነች። ዮናስም የጥፋት ትንቢቱ ተፈጻሚነት ሳያገኝ በመቅረቱ አኰረፈ። መጽሐፉ እግዚአብሔር በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለው ያስረዳል፤ ይልቁንም እግዚአብሔር የፍቅርና የምሕረት አምላክ በመሆኑ የሕዝቡን ጠላቶች ከሚቀጣና ከሚደመስስ ይልቅ ይቅር ሊላቸውና ሊያድናቸው እንደሚወድ ያስረዳል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የዮናስ ከጌታ መሸሽ (1፥1-16)
የዮናስ ጸሎት (2፥1-11)
የዮናስ ወደ ነነዌ መሄድና የሕዝቡ ንስሓ (3፥1-10)
እግዚአብሔር ባደረገው ምሕረት ዮናስ መበሳጨቱ (4፥1-11)
ምዕራፍ

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ