የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢያሱ 14

14
በስተ ምዕራብ የሚገኘውን የዮርጋኖስ ግዛት ክፍፍል
1 # ኢያ. 17፥4፤ 21፥1፤ ዘኍ. 27፥19-22፤ 34፥17-18። የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት፥ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያከፋፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤ 2#ዘኍ. 26፥55፤ 33፥54፤ 34፥13።ጌታ በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አከፋፈሉአቸው። 3#ኢያ. 13፥8፤14፤33።ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበረ፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም። 4#ኢያ. 21፥3-40፤ ዘፍ. 48፥5።የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን ማሰማርያ በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። 5ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ፥ ምድሪቱንም ተካፈሉ።
ለካሌብ ኬብሮን እንደ ርስት መሰጠቱ
6 # ዘኍ. 14፥24፤ 30፤ 32፥12፤ ዘዳ. 1፥36፤38። የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ ጌታ በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። 7#ዘኍ. 14፥6-9።የጌታ ባርያ ሙሴ ምድሪቱን እንድሰልል ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ጎልማሳ ነበርሁ እኔም ተመልሼ በልቤ የነበረውን ቃል ተናገርሁ። 8#ዘኍ. 13፥31-33፤ 14፥24፤ 32፥12፤ ዘዳ. 1፥36።ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን ጌታን ፈጽሜ ተከተልሁ። 9#ዘኍ. 14፥24።ሙሴም በዚያ ቀን እንዲህ ብሎ ማለ፦ ‘አምላኬን ጌታን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም በእርግጥ ርስት ይሆናል።’ 10#ዘኍ. 14፥30።እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ ጌታ ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረው ጌታ እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ፤ እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ እኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ። 11#ሲራ. 46፥1-10።ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ እንዲሁ ዛሬም ብርቱ ነኝ፤ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው። 12#ኢያ. 11፥21-22።አሁን እንግዲህ በዚያን ቀን ጌታ የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔናቃውያን ታላላቆችና የተመሸጉ ከተሞችም በዚያ እንዳሉ ሰምተህ ነበር፤ ምናልባት ጌታ ከእኔ ጋር ይሆናል፥ ጌታም እንደ ተናገረኝ አሳድዳቸዋለሁ።”
13 # ኢያ. 10፥36-37፤ 15፥13-19፤ 21፥11-12። ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው። 14ስለዚህም የእስራኤል አምላክ ጌታን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነች። 15#መሳ. 1፥10።የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት-አርባቅ ትባል ነበር፤ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ታላቅ ሰው ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ