የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢያሱ 15

15
የይሁዳ ግዛት
1 # ዘኍ. 34፥3። የይሁዳም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ይደርሳል። 2#ዘኍ. 34፥3-12።በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ ትይዮ እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ። 3ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥ 4ወደ ዓጽሞንም አለፈ፥ በግብጽም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። 5በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤ 6#ኢያ. 18፥18-19፤ 22።ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤትሖግላ ወጣ፥ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወጣ፤ 7#ኢያ. 7፥26፤ 18፥16-18።ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በሸለቆው በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ታጠፈ፤ ድንበሩም ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ ማብቂውም በዓይንሮጌል አጠገብ ነበረ፤ 8#ኢያ. 18፥16።ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፤ 9#ኢያ. 18፥15።ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤ 10ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። 11ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ ወደ ሽክሮን ታጠፈ፤ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤልም በኩል ወጣ፤ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። 12በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
ካሌብ ድርሻውን መያዙ
13 # መሳ. 1፥10-15። ጌታም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።#ኢያ. 14፥13-15። 14#ዘኍ. 13፥22፤ መሳ. 1፥20።ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ከዚያ ስፍራ አሳደደ። እነዚህም የዓናቅ ትውልድ ነበሩ። 15#ኢያ. 10፥38።ከዚያም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበረ። 16ካሌብም፦ “ቂርያትሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ” አለ። 17የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፤ ስለዚህ ካሌብ ልጁን ዓክሳንን አጋባው። 18እርሷም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፤ እርሷም ከአህያዋ ወረደች፤ ካሌብም፦ “ምን ፈለግሽ?” አላት። 19እርሷም እንዲህ አለችው፦ “በረከትን ስጠኝ፤ በደቡብም በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ።” እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።
የይሁዳ ከተሞች
20በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው።
21በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቀብሴኤል፥ ዔደር፥ ያጉር፥ 22ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥ 23ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን፥ 24ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት፥ 25ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥ 26አማም፥ ሽማዕ፥ ሞላዳ፥ 27ሓጸርጋዳ፥ ሐሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥ 28ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥ 29በኣላ፥ ዒዪም፥ ዓጼም፥ 30ኤልቶላድ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥ 31ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥ 32ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዐይን፥ ሪሞን፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
33በቈላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥ 34ዛኖዋ፥ ዓይንገኒም፥ ታጱዋ፥ ዓይናም፥ 35የርሙት፥ ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥ 36ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፤ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
37ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ 38ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥ 39ለኪሶ፥ ቦጽቃት፥ ዔግሎም፥ 40ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ 41ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
42ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን፥ 43ይፍታሕ፥ አሽና፥ ንጺብ፥ 44ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፤ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
45አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፤ 46ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕሩ ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር።
47አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብጽ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።
48በተራራማው አገር ሳምር፥ የቲር፥ ሶኮ፥ 49ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና፥ 50ዓናብ፥ ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥ 51ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
52አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ 53ያኒም፥ ቤትታጱዋ፥ አፌቃ፥ 54ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያት-አርባቅ፥ ጺዖር፤ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
55ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥ 56ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥ 57ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው።
58ሐልሑል፥ ቤትጹር፥ ጌዶር፥ 59ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን፤ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
60 # ኢያ. 18፥14። ቂርያት-ይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
61በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ፥ 62ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፤ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
63 # መሳ. 1፥21፤ 2ሳሙ. 5፥6። በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ