ኦሪት ዘሌዋውያን 1
1
የሚቃጠል መሥዋዕት
1 #
ዘፀ. 40። ጌታም ሙሴን ጠርቶ ከመገናኛው ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ 2#ዘሌ. 1፥3፤ 10፤ 3፥1፤ 6፤ 12።“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለጌታ መባ ሲያቀርብ፥ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከሆኑ ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ ታቀርባላችሁ።
3 #
ዘሌ. 6፥1-6፤ 22፥18-19። “መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።#ዘሌ. 22፥17-25፤ ዘፀ. 12፥5። 4#ዘሌ. 3፥2፤ 8፤ 13፤ 4፥4፤ 15፤ 24፤ 8፥14፤ 18፤ 22፤ ዘኍ. 8፥12፤ 2ዜ.መ. 29፥23፤ ዘሌ. 16፥21፤ 24፥14፤ ዘኍ. 27፥18፤ 23፤ ዘዳ. 34፥9።እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ የእርሱንም ኃጢአት ለማስተስረይ የሠመረ ይሆንለታል።#ዘሌ. 19፥5፤ 22፥19-29፤ ዘፍ. 4፥3-5፤ ሚል. 1፥8-14።#ዘሌ. 9፥7፤ 14፥20፤ ኢዮብ 1፥5፤ 42፥8፤ ዘፍ. 32፥21፤ ዘፀ. 29፥36-37፤ 30፥15፤ ዘሌ. 16፥16-20፤ 17፥11፤ ሕዝ. 43፥20፤ 26። 5#ዘሌ. 1፥11፤ 15፤ 3፥2፤ 8፤ 13፤ ዘሌ. 4፥5-7፤ 25።በሬውንም በጌታ ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። 6የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ይገፍፈዋል፥ በየብልቱም ይቈርጠዋል። 7የካህኑም የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሳት ያነድዳሉ፥ በእሳቱም ላይ እንጨት ይደረድራሉ፤ 8የአሮንም ልጆች ካህናቱ ብልቶቹንና ራሱን ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤ 9#ዘሌ. 2፥2፤ 3፥5፤ 4፥31፤ 26፥31፤ ዘፍ. 8፥20-21፤ ዘኍ. 28፥2፤ ዘሌ. 3፥11፤ 21፥6፤21፤ 22፥25።የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በእሳትም የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ሁሉንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
10“የእርሱም ቁርባን ለሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል። 11በመሠዊያውም አጠገብ በስተ ሰሜን በኩል በጌታ ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። 12እንዲሁም ከራሱና ከስቡ ጋር አብሮ በየብልቱ ይቈርጠዋል፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርበዋል፤ 13የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል። ካህኑም ሁሉን ያቀርበዋል፤ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን፥ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
14 #
ዘሌ. 5፥7፤ 12፥8፤ 15፥14-15፤ ሉቃ. 2፥24። “ለጌታም የሚቀርበው ቁርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከወፎች ቢሆን፥ ቁርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል። 15#ዘሌ. 5፥8-9።ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፤ ራሱንም ይቈለምመዋል፤ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል። ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፈጠፋል፤ 16የሆድ ዕቃውንም ከላባዎቹ ጋር ለይቶ በመሠዊያው አጠገብ በስተ ምሥራቅ በኩል ባለው በአመዱ ስፍራ ይጥለዋል፤ 17ክንፎቹንም ይዞ በመነጠል ይቀድደዋል እንጂ አይከፍለውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን፥ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘሌዋውያን 1: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ