የሉቃስ ወንጌል 11
11
ኢየሱስ ስለ ጸሎት ማስተማሩ
(ማቴ. 6፥9-13፤ 7፥7-11)
1እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንዲሁ መጸለይን አስተምረን፤” አለው። 2ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በማናቸውም ጊዜ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባት ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ 3የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤ 4ኀጢአታችንንም ይቅር በለን፤ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር እንላለንና፤ ወደ ፈተናም አታግባን።’ ”
5እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ ማን ይሆን ወዳጅ ኖሮት፥ በእኩለ ሌሊት ወደ እርሱ ሄዶ እንዲህ የሚለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ! ሦስት እንጀራ አበድረኝ፤ 6አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት ምንም የለኝምና’፤ 7ያም ከውስጥ መልሶ፦ ‘አታስቸግረኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ናቸው፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም፤’? 8እላችኋለሁ፤ ወዳጁ ስለ ሆነ እንኳ ተነሥቶ ባይሰጠው፥ ስለ ንዝነዛው ግን ተነሥቶ የሚፈልገውን ያህል ይሰጠዋል። 9እኔም እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ 10የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል። 11አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ ዓሣ ቢለምነው፥ በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? 12ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? 13እንግዲያውስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው!”
ዓይነ ስውርና መናገር የተሳነው ጋኔን ስለያዘው ሰው
(ማቴ. 12፥22-30፤ ማር. 3፥20-27)
14መናገርም የተሳነውን ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣ በኋላ መናገር የተሳነው ሰው ተናገረ፥ ሕዝቡም ተደነቁ፤ 15#ማቴ. 9፥34፤ 10፥25።ከእነርሱ ዘንድ አንዳንዶች ግን፦ “በብዔልዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ። 16#ማቴ. 12፥38፤ 16፥1፤ ማር. 8፥11።ሌሎችም ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ይፈልጉ ነበር። 17ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሱ የተለያየ መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ ቤትም በቤት ላይ ይወድቃል። 18ሰይጣንም ደግሞ እርስ በርሱ ቢለያይ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እኔ አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ እናንተ ብላችኋልና፤ 19እኔስ በብዔልዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ፥ ልጆቻችሁ በማን ያስወጣሉ? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። 20እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥቷል። 21በማናቸውም ጊዜ ኀይለኛ ሰው በሚገባ የጦር ዕቃውን ታጥቆ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ንብረቱ በሰላም የተጠበቀ ይሆናል፤ 22ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ አደጋ ጥሎበት ካሸነፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን የጦር ዕውቃን ይወስድበታል፤ ምርኮውንም ያካፍላል። 23#ማር. 9፥40።ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋርም የማይሰበስብ ይበትናል።
ስለ ርኩሳን መናፍስት
24“ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍትን ፈልጎ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ ባለማግኘቱ ግን፦ ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ፤’ ይላል፤ 25ሲመጣም ተጠርጎና ተስተካክሎ ያገኘዋል። 26በዚያም ጊዜ ሄዶ ከእርሱ የባሱ ክፉ ሌሎች ሰባት መናፍስትን ከእርሱ ጋር ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ የዚያም ሰው ሁኔታ ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ይሆናል።”
እውነተኛ ደስታ
27ኢየሱስም ይህንን በመናገር ላይ ሳለ፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦ “የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው፤” አለችው። 28እርሱ ግን፦ “በእርግጥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው፤” አለ።
ምልክትን ስለ ጠየቁ ሰዎች
(ማቴ. 12፥38-42)
29 #
ማቴ. 16፥4፤ ማር. 8፥12። ሕዝብም በብዛት እየተሰበሰቡ በነበሩ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክትን ይፈልጋል፤ ከዮናስም ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። 30#ዮናስ 3፥4።ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። 31#1ነገ. 10፥1-10፤ 2ዜ.መ. 9፥1-12።ንግሥተ አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ትነሳለች፥ በእነርሱም ላይ ትፈርዳለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ። 32#ዮናስ 3፥5።የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሳሉ፥ በእርሱም ላይ ይፈርዳሉ፤ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ።
የሰውነት መብራት
(ማቴ. 5፥15፤ 6፥22-23)
33 #
ማቴ. 5፥15፤ ማር. 4፥21፤ ሉቃ. 8፥16። “መብራትንም አብርቶ በስውር ቦታ ወይም ከእንቅብ በታች የሚያኖረው ማንም የለም፤ የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል እንጂ። 34የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ነው። ዐይንህ ጤናማ በሆነ ጊዜ ሰውነትህ ሁሉ ደግሞ በብርሃን የተመላ ይሆናል። ዐይንህ ታማሚ በሆነ ጊዜ ግን ሰውነትህ ደግሞ በጨለማ የተመላ ይሆናል። 35ስለዚህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳልሆነ በልብህ አስተውል። 36እንግዲህ ሰውነትህ ሁሉ በብርሃን የተመላ፥ ጨለማም የሆነ የአካል ክፍል የሌለው ከሆነ፥ መብራት በፀዳሉ ብርሃን እንደሚሰጥህ እንዲሁ ሰውነትህ ሁሉ በብርሃን የተመላ ይሆናል።”
ፈሪሳውያንና የሙሴ ሕግ መምህራን መወቀሳቸው
(ማቴ. 23፥1-36፤ ማር. 12፥38-40)
37ይህንንም በመናገር ላይ በነበረ ጊዜ አንድ ፈሪሳዊ ከእርሱ ጋር ምሳ እንዲበላ ለመነው፤ ኢየሱስም ወደ እርሱ ገብቶ ተቀመጠ። 38ከምሳም በፊት አስቀድሞ እንዳልታጠበ በማየቱ ፈሪሳዊው ተደነቀ። 39ጌታም እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል። 40እናንተ ሞኞች! የውጭውን የፈጠረ እርሱ የውስጡንስ ደግሞ አለፈጠረምን? 41ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።
42 #
ዘሌ. 27፥30። “ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከአዝሙድና ከጤና አዳም ከአትክልትም ሁሉ አሥራት ታወጣላችሁ፤ ፍርድንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ግን ቸል ትላላችሁ፤ ይልቁንስ እነዚያን ደግሞ ሳትተዉ እነዚህን ማድረግ ይገባችሁ ነበር። 43እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኵራቦች የከበሬታን ወንበርንና በገበያ ቦታዎች ሰላምታን ትወዳላችሁና። 44እናንተ ወዮላችሁ! ሰዎች ሳያውቋቸው በላያቸው የሚሄዱባቸው የተሰወሩ መቃብሮች ትመስላላችሁና።”
45ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ “መምህር ሆይ! ይህን ስትል እኮ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው፤” አለው። 46እርሱም እንዲህ አለ፦ እናንተ ሕግ አዋቂዎች ደግሞ ወዮላችሁ! ለመሸከም ከባድ የሆነውን ሸክም ሰዎችን ታሸክማላችሁ፥ ራሳችሁ ግን በአንዲት ጣታችሁ እንኳ ሸክሙን አትነኩትምና። 47እናንተ ወዮላችሁ!አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብሮች ትሠራላችሁና። 48እንግዲህ በአባቶቻችሁ ሥራ ትስማማላችሁ፤ ስለ እርሱም ትመሰክራላችሁ፤ እነርሱ ገደሉአቸው እናንተ ደግሞ መቃብሮቻቸውን ትሠራላችሁና። 49ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ “ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም፤ 50ስለዚህም ይህ ትውልድ ተጠያቂ የሚሆነው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በፈሰሰው በነቢያት ሁሉ ደም፥ 51#ዘፍ. 4፥8፤ 2ዜ.መ. 24፥20፤21።ይህም ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ ነው። አዎን እላችኋለሁ፤ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል። 52እናንተ ሕግ አዋቂዎች ወዮላችሁ! የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችኋልና፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁም፤ የሚገቡትንም ከለከላችሁ።” 53እርሱም ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ላይ ሳለ ጻፎችና ፈሪሳውያን እርሱን እጅግ በመቃወም ስለ ብዙ ነገሮች የትንኮሳን ጥያቄ ይጠይቁት ጀመር፤ 54በዚህም እርሱ ከሚናገረው አንድ ነገርን ለማጥመድ አደቡበት።
Currently Selected:
የሉቃስ ወንጌል 11: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ