የሉቃስ ወንጌል 8
8
ኢየሱስን ይከተሉ የነበሩ ሴቶች
1ከዚህም በኋላ ኢየሱስ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እያበሠረ በየከተማውና በየመንደሩ ያልፍ ነበር፤ ዐሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ 2#ማቴ. 27፥55፤56፤ ማር. 15፥40፤41፤ ሉቃ. 23፥49።ከክፉዎች መናፍስትና ከደዌም ተፈውሰው የነበሩ አንዳንድ ሴቶች፤ ከእነርሱም፦ ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የምትባል ማርያም፥ 3የሄሮድስ መጋቢ የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስናና ብዙዎች ሌሎችም ሆነው ከንብረታቸው በመጠቀም ያገለግሉአቸው ነበር።
የዘሪው ምሳሌ
(ማቴ. 13፥1-9፤ ማር. 4፥1-9)
4ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበና ከየከተማውም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ እንዲህ ሲል በምሳሌ ተናገረ፦ 5“ዘሪ ዘሩን ለመዝራት ወጣ። በሚዘራበትም ጊዜ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፤ ተረገጠም፤ የሰማይ ወፎችም ጨረሱት። 6ሌላውም በዐለት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ እርጥበት ስላልነበረው ደረቀ። 7ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፤ እሾሁም አብሮ በቀለና አነቀው። 8ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ መቶ እጥፍ አፈራ።” ይህንንም እየተናገረ፦ “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፤” ብሎ ጮኸ።
የዘሪው ምሳሌ ትርጒም
(ማቴ. 13፥18-23፤ ማር. 4፥13-20)
9ደቀ መዛሙርቱም፦ “ይህ ምሳሌ ትርጓሜው ምንድነው?” ብለው ጠየቁት። 10#ኢሳ. 6፥9።እርሱም “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌዎች ይነገራቸዋል” አላቸው። 11“የምሳሌውም ትርጒም ይህ ነው፦ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው። 12በመንገድ ዳርም ያሉት የሰሙት ናቸው፤ ከዚያ በኋላም አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል። 13እንዲሁም በዐለት ላይ ያሉት ቃሉን በሰሙ ጊዜ በደስታ የሚቀበሉት ናቸው፤ ነገር ግን ሥር የላቸውም፥ እነርሱም ለጊዜው ብቻ ያምናሉ እንጂ በፈተና ጊዜ ይክዳሉ። 14በእሾህም መካከል የወደቁት እንዲሁ ከእነዚያ ከሰሙት ወገን ናቸው፤ በመንገዳቸውም በዚህ የምድራዊ ሕይወት ምኞትና ሀብት እንዲሁም ምቾት ይታነቃሉ፤ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። 15በመልካም መሬት ላይ ያሉት ደግሞ ቃሉን በመልካምና በቅን ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፥ በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።
16 #
ማቴ. 5፥15፤ ሉቃ. 11፥33። “መብራትንም አብርቶ በእንቅብ የሚከድነው ወይም ከአልጋ በታች የሚያኖረው ማንም የለም፤ ይልቅስ የሚገቡት ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል። 17#ማቴ. 10፥26፤ ሉቃ. 12፥2።የማይገለጥ ምንም የተሰወረ የማይታወቅም ወደ ብርሃንም የማይመጣ ምንም የተሸሸገ ነገር የለምና። 18#ማቴ. 25፥29፤ ሉቃ. 19፥26።ስለዚህ እንዴት እንደምትሰሙ በጥንቃቄ አጢኑ፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ሁሉ፥ ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።”
የኢየሱስ እናት እና ወንድሞቹ
(ማቴ. 12፥46-50፤ ማር. 3፥31-35)
19እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፤ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት አልቻሉም። 20እንዲህም ተብሎ ተነገረው፦ “እናትህና ወንድሞችህ ሊያዩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል።” 21እርሱም መልሶ፦ “እናቴና ወንድሞቼ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው፤” አላቸው።
ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ ማድረጉ
(ማቴ. 8፥23-27፤ ማር. 4፥35-41)
22ከዕለታቱም በአንዱ ቀንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ “ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ። 23እየሄዱም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። ዓውሎ ነፋስም በሐይቁ ላይ ተነሣ፤ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበር፤ እነርሱም በአደጋ ላይ ስለ ነበሩ ተጨንቀው ነበር። 24ቀርበውም፦ “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! እየጠፋን ነው፤” እያሉ ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚናውጠውን የውኃ ሞገድ ገሠጻቸው፤ እነርሱም አቆሙ፤ ጸጥታም ሆነ። 25እርሱም፦ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። በፍርሃትና በመደነቅ ተውጠውም፤ እርስ በርሳቸው፦ “እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን ሳይቀር የሚያዝ፥ እነርሱም የሚታዘዙለት ይህ ለመሆኑ ማን ነው?” ተባባሉ።
ኢየሱስ በጌርጌሴኖን ጋኔን ያደረበትን ሰው መፈወሱ
(ማቴ. 8፥28-34፤ ማር. 5፥1-20)
26በገሊላም ማዶ ወዳለችው ወደ ጌርጌሴኖን አገር ተሻገሩ። 27እርሱም ወደ ምድር እንደ ወረደ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ለረጅም ጊዜ ልብስ አይለብስም ነበር፥ በመቃብሮች እንጂ በቤት ውስጥም አይኖርም ነበር። 28ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፦ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ? እንዳታሰቃየኝ እለምንሃለሁ፤” አለ። 29እንዲህም የሆነው ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ከሰውዬው እንዲወጣ አዞት ስለ ነበረ ነው። ለብዙም ጊዜ ይዞት ነበርና፤ በሰንሰለትና በእግር ብረትም ታስሮ ይጠበቅ ነበር፤ እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይወሰድ ነበር። 30ኢየሱስም፦ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙዎች አጋንንት ገብተውበት ነበርና፦ “ሌጌዎን” አለው። 31ወደ ጥልቁም ሂዱ ብሎ እንዳያዛቸው ለመኑት። 32በዚያም በኮረብታው ዳርቻ ላይ የብዙ ዐሣማዎች መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ ወደ እነርሱም ለመግባት እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ ፈቀደላቸውም። 33አጋንንቱም ከሰውዬው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ሐይቁ ተጣድፎ በመውረድ ሰጠመ።
34እረኞቹም የሆነውን ባዩ ጊዜ ሸሽተው በከተማውና በገጠሩ አወሩት። 35ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ፥ ልቡም ተመልሶ፥ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ። 36ያዩትም ደግሞ አጋንንት ያደሩበት ሰው እንዴት እንደ ዳነ አወሩላቸው። 37በጌርጌሴኖንም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች የሚኖረው ሕዝብ ሁሉ በታላቅ ፍርሃት ተይዘው ስለ ነበር ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት፤ እርሱም በታንኳ ገብቶ ተመለሰ። 38አጋንንትም የወጡለት ሰው ከእርሱ ጋር እንዲሆን ለመነው፤ ኢየሱስ ግን እንዲህ ብሎ አሰናበተው፦ 39“ወደ ቤትህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ተናገር።” እርሱም በመላው ከተማ ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት እየሰበከ ሄደ።
ስለ ኢያኢሮስ ልጅ እና ደም ይፈሳት ስለ ነበረች ሴት
(ማቴ. 9፥18-26፤ ማር. 5፥21-43)
40ሕዝቡም ሁሉ እየጠበቁት ስለ ነበር ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ተቀበሉት። 41እነሆም፥ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው መጣ፤ እርሱም የምኵራብ አለቃ ነበረ፤ በኢየሱስም እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ለመነው፤ 42ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርሷም ለመሞት እያጣጣረች ነበር። ሲሄድም ሕዝቡ በዙርያው እየተጋፉት ያጨናንቁት ነበር። 43ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። 44ከበስተኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ወዲያውም ደምዋ መፍሰሱን አቆመ። 45ኢየሱስም፦ “ማን ነው የነካኝ?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስ፦ “አቤቱ! ሕዝቡ በዙሪያህ ከበውህ እየተጋፉህ እኮ ነው!” አለ። 46ኢየሱስ ግን፦ “አንድ ሰው ዳስሶኛል፤ ከእኔ ኃይል መውጣቱን አውቄአለሁና፤” አለ። 47ሴቲቱም መደበቅ እንዳልቻለች ባወቀች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ በምን ምክንያት እንደ ዳሰሰችውና እንዴት ፈጥና እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች። 48እርሱም፦ “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤” አላት።
49እርሱም ይህን እየተናገረ ሳለ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም፤” አለ። 50ኢየሱስ ግን ይህን ሰምቶ ለኢያኢሮስ መልሶ እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ እርሷም ትድናለች።” 51ወደ ቤቱም በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስና ከያዕቆብ ከዮሐንስም፥ ከልጅቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር እንዲገባ አልፈቀደም። 52ሁሉም እያለቀሱ ደረታቸውን ይመቱላት ነበር። እርሱ ግን፦ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም፤” አለ። 53እንደ ሞተችም ስላወቁ በጣም ሳቁበት። 54እርሱ ግን እጅዋን ይዞ፦ “አንቺ ልጅ! ተነሺ፤” ብሎ ተጣራ። 55መንፈሷም ተመለሰች፤ ፈጥናም ተነሣች፤ የምትበላውም ነገር እንዲሰጣት አዘዘ። 56ወላጆችዋም ተገረሙ፤ እርሱ ግን የሆነውን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።
Currently Selected:
የሉቃስ ወንጌል 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ