የማቴዎስ ወንጌል 8
8
ኢየሱስ ለምጻሙን ሰው እንደ ፈወሰ
(ማር. 1፥40-45፤ ሉቃ. 5፥12-16)
1ከተራራው በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። 2እነሆ አንድ ለምጻም መጥቶ ሰገደለትና “ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” አለው። 3እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ። 4#ዘሌ. 14፥1-32።ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።
ኢየሱስ የመቶ አለቃውን አገልጋይ እንደ ፈወሰ
(ሉቃ. 7፥1-10)
5ወደ ቅፍርናሆም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ በመለመን፥ 6“ጌታ ሆይ! ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሠቃየ በቤት ተኝቶአል” አለው። 7ኢየሱስም “እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው። 8የመቶ አለቃውም እንዲህ ሲል መለሰ “ጌታ ሆይ! ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል። 9#ባሮክ 3፥33-35።እኔ ራሴ ከባለሥልጣኖች በታች ነኝ፤ ከእኔ በታች ደግሞ ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን ‘ሂድ’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን ደግሞ ‘ና’ ስለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም ‘ይህን አድርግ’ ስለው ያደርጋል።” 10ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ይከተሉት የነበሩትን እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም። 11#ሉቃ. 13፥29።እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃም፥ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋርም በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤ 12#ማቴ. 22፥13፤ 25፥30፤ ሉቃ. 13፥28።የመንግሥቱ ልጆች ግን ውጪ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” 13ኢየሱስም ለመቶ አለቃው “ሂድና እንደ እምነትህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።
ኢየሱስ ብዙዎችን ከደዌ እንደ ፈወሰ
(ማር. 1፥29-34፤ ሉቃ. 4፥38-41)
14ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ አማቱ በትኩሳት ታማ ተኝታ አያት፤ 15እጅዋን ዳሰሳት፤ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለችው። 16በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደሩባቸው ብዙ ሰዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ መናፍስቶቹን ሁሉ በቃል አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። 17#ኢሳ. 53፥4።ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸከመ፤” የተባለው እንዲፈጸም ነው።
ኢየሱስን ለመከተል ስለ ጠየቁ ሰዎች
(ሉቃ. 9፥57-62)
18ኢየሱስ ብዙ ሰዎች በአጠገቡ ሲሰበሰቡ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። 19አንድ ጸሐፊ መጥቶ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው። 20ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጉድጓድ፥ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት የለውም፤” አለው። 21#ጦቢ. 4፥3፤4።ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ “ጌታ ሆይ! መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለው። 22ኢየሱስም “ተከተለኝ፤ ሙታንን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤” አለው።
ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ እንዳደረገ
(ማር. 4፥35-41፤ ሉቃ. 8፥22-25)
23ወደ ጀልባ በገባ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ተከተሉት። 24እነሆ ማዕበሉ ጀልባይቱን እስኪሸፍናት ድረስ በባሕሩ ላይ ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። 25ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! ልንጠፋ ነው፥ አድነን፤” እያሉ ቀሰቀሱት። 26እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸው፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። 27ሰዎቹም “ነፋሳትና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት፥ ይሄ ማነው?” እያሉ ተደነቁ።
ኢየሱስ በአጋንንት የተያዙ ሰዎችን እንደ ፈወሰ
(ማር. 5፥1-20፤ ሉቃ. 8፥26-29)
28ወደ ማዶ ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ስፍራ ወጥተው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስከማይችል ድረስ እጅግ አደገኞች ነበሩ። 29እነሆ እንዲህ እያሉ ጮኹ “የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?” 30ከእነርሱም ርቆ ብዙ የዓሣማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር። 31አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ፥ ወደ ዓሣማው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። 32እርሱም “ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወጥተው ወደ አሣማዎቹ ሄደው ገቡ፤ እነሆ የዓሣማዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር ሮጡ፥ በውኆቹ ውስጥ ሰጥመው ሞቱ። 33እረኞቹም ሸሹ፤ ወደ ከተማይቱም ሄደው ነገሩን ሁሉ አጋንንትም አድረውባቸው በነበሩት ሰዎች የሆነውን አወሩ። 34እነሆ ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድ ለመኑት።
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ