የማርቆስ ወንጌል መግቢያ
መግቢያ
የማርቆስ ወንጌል “ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ የምሥራች ቃል መጀመሪያ ነው” በማለት ይጀምራል። የማርቆስ ወንጌል በአንድ በኩል የኢየሱስን ማንነት ከተለያየ አቅጣጫ ያሳያል፤ ለእግዚአብሔርና ለወንጌል ጸሐፊው ኢየሱስ መሢሕ ነው። አጋንንት የእግዚአብሔር ቅዱስ ብለው ይጠሩታል። ሕዝቡ የዮሴፍና የማሪያም ልጅ ይለዋል። ፈሪሳዊያን ሥልጣኑን በመካድ በብኤል ዘቡል እንደሚሠራ ይናገራሉ። ከሐዋርያት መካከል ጴጥሮስ መሢሕ ይለዋል። በሚሰቀልበት ጊዜ ሮማዊው መቶ አለቃ ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር ይላል። እንግዲህ የማርቆስ ወንጌል ኢየሱስን ለማወቅ ከገሊላ እስከ ኢየሩሳሌም፥ እስከ ጎልጎታን እስክ እስከ ሞቱ ድረስ መከተል እንደሚያስፈልግ ይገልጻል። በሌላ አነጋገር የኢየሱስን ማንነት ከሕማማቱ፥ ከሞቱና ከትንሣኤው ነጥለን ማየት አንችልም።
በማርቆስ ወንጌል ውስጥ ያሉትን የማንነት ጥያቄዎች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ማስረጃዎች ማየት እንችላለን፦ “ይህ ምንድነው? ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው?” (1፥27)፤ “ይህ ሰው ስለምን እንደዚህ ይናገራል? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” (2፥7)፤ “ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” (4፥41)፤ “እናንተሳ ማን ትሉኛላችሁ?” (8፥29) ሌሎችም እነዚህን የሚመሳስሉ ጥያቄዎችን ማስተዋል ይቻላል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የኢየሱስ አገልግሎት ዝግጅት (1፥1-13)
የኢየሱስ የማንነት ምሥጢር (1፥14—8፥26)
የኢየሱስ ማንነት እየተገለጠ መምጣቱ (8፥27—9፥32)
የተልእኮው ሙሉ ምሥጢር መገለጥ (9፥33—16፥8)
ከሞት የተነሣው ጌታ መገለጥና ዕርገቱ (16፥9-20)
ምዕራፍ
Currently Selected:
የማርቆስ ወንጌል መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ