ኦሪት ዘኍልቊ 17
17
የአሮን በትር ማቈጥቈጡ
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“ለእስራኤል ልጆች ተናገር፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ሁሉ ከየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ። 3በሌዊም በትር ላይ የአሮንን ስም ጻፍ። ለእያንዳንዱ ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ አንድ በትር ይኖራቸዋልና። 4እኔ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራቸው። 5እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቁጣለች፥ በእናንተም ላይ ያጉረመረሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” 6ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ እያንዳንዱም አለቃ በየአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር፥ ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። 7ሙሴም በትሮቹን በጌታ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው።
8 #
ዕብ. 9፥4። እንዲህም ሆነ፤ በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነው የአሮን በትር አቈጥቁጦ፥ እምቡጥም አውጥቶ፥ አበባም አብቦ፥ የበሰለ ለውዝም አፍርቶ ነበር። 9ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከጌታ ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፥ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። 10ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልሰህ አኑር፤ እርሱም ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆኖ ይቀመጥ፤ እነርሱም እንዳይሞቱ በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን ታስቆምበታለህ።” 11ሙሴም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ እንዳዘዘው እንዲሁ እርሱ አደረገ።
12የእስራኤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እነሆ፥ እንሞታለን፥ እንጠፋለን፥ ሁላችንም እንጠፋለን። 13ፈጽሞ ወደ ጌታ ማደሪያ የሚቀርብ ሁሉ፥ ይሞታል፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለንን?”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቊ 17: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ