ኦሪት ዘኍልቊ 28
28
በየቀኑ የሚቀርብ መሥዋዕት
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ “‘ማዕዴን፥ ለእኔ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባኔን፥ መባዬን በተገቢው ጊዜ እንድታቀርቡልኝ በጥንቃቄ ልብ በሉ።’ 3እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። 4አንዱን ጠቦት በማለዳ፥ ሌላውንም ጠቦት በማታ አቅርብ፤ 5የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን ታቀርባለህ። 6ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በሲና ተራራ ላይ ተሰናድቶ በእሳት የቀረበ የዘወትር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። 7የመጠጡ ቁርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ይሁን፤ በመቅደሱ ውስጥ ለጌታ ለመጠጥ ቁርባን መጠጥ አፍስስ። 8ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባለህ፤ የእህሉን ቁርባንና የመጠጡን ቁርባን በማለዳ እንዳቀረብህ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ።’
የሰንበት ቁርባን
9“በሰንበትም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ለእህልም ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ የመጠጡንም ቁርባን ታቀርባላችሁ። 10ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።
በየወሩ የሚቀርብ ቁርባን
11“በወሩም መባቻ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ሁለት ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤ 12እንዲሁም ደግሞ ለእያንዳንዱም ወይፈን ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ አውራ በግም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ 13ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ። 14የመጠጥ ቁርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። 15ለጌታም ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል።
የፋሲካ ቁርባን
16 #
ዘፀ. 12፥1-13፤ ዘዳ. 16፥1፤2። “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን የጌታ ፋሲካ ነው። 17#ዘፀ. 12፥14-20፤ 23፥15፤ 34፥18፤ ዘዳ. 16፥3-8።ከዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው ቂጣ ይበላል። 18በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል፤ በእርሱም የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። 19ለጌታም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ፤ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፤ እነርሱም ነውር የሌለባቸው መሆናቸውን ተመልከቱ። 20የእህል ቁርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 21ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ። 22ማስተስረያ እንዲሆንላችሁ አንድ አውራ ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባላችሁ። 23ማልዶ ከሚቀርበው ዘወትር ከሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ እነዚህን ታቀርባላችሁ። 24ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን የቁርባኑን ማዕድ ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል። 25በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።
የሰባቱ ሱባዔ የዓል ቁርባን
26 #
ዘፀ. 23፥16፤ 34፥22፤ ዘዳ. 16፥9-12። “ደግሞ በበኵራት ቀን ከሰባቱ ሱባዔ በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቁርባን ለጌታ ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። 27ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ 28ለእህል ቁርባናቸው በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለእያንዳንዱ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአንዱም አውራ በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 29ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ። 30ማስተስረያ እንዲሆንላችሁ አንድ አውራ ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባላችሁ። 31ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን ሌላ እነርሱንና የመጠጥ ቁርባናቸውን ታቀርባላችሁ፤ እነርሱም ነውር የሌለባቸው መሆናቸውን ተመልከቱ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቊ 28: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ