ኦሪት ዘኍልቊ 36
36
የሴት ወራሾች ጋብቻ
1ከዮሴፍ ልጆች ወገኖች የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ወገን አለቆች ቀረቡ፥ በሙሴና በእስራኤልም ልጆች አባቶች አለቆች ፊት ተናገሩ፤ 2#ዘኍ. 27፥7።እነርሱም እንዲህ አሉ፦ “ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርገህ በዕጣ ከፋፍለህ እንድትሰጣቸው ጌታ አንተን ጌታችንን አዘዘህ፤ ጌታም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አንተን ጌታችንን አዘዘ። 3ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይወሰዳል፥ እነርሱም ወደ አሉበት ወደ ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም ከርስታችን ዕጣ ይወሰዳል። 4ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በመጣ ጊዜ ርስታቸው እነርሱ ወደ አሉበት ነገድ ርስት ይጨመራል፤ ርስታቸውም ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይወሰዳል።”
5ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንደ ጌታ ቃል እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “የዮሴፍ ልጆች ነገድ እውነት የሆነን ነገር ተናግረዋል። 6ጌታ ስለ ሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ ‘የወደዱትን ያግቡ፤ ነገር ግን ከአባታቸው ወገን ከሆነ ነገድ ብቻ ያግቡ። 7ስለዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ የአባቶቹን ነገድ ርስት ይያዝ። 8ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ሰው የአባቶቹን ርስት እንዲወርስ፥ ከማናቸውም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአባትዋ ነገድ ባል ታግባ። 9ስለዚህም ከአንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይተላለፍ ከእስራኤልም ልጆች ነገድ እያንዳንዱ የራሱን ርስት ይያዝ።’ ”
10ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። 11የሰለጰዓድ ልጆች ማህለህ፥ ቲርጻ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ኑዓ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። 12ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ልጆች ወገኖች ባሎቻቸውን አገቡ፥ ርስታቸውም በአባታቸው ነገድ ጸና።
13ጌታ በሙሴ አንደበት የእስራኤልን ልጆች በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ሜዳ ያዘዛቸው ትእዛዝና ፍርድ እነዚህ ናቸው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቊ 36: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ