መጽሐፈ ምሳሌ 12
12
1 #
ሲራ. 21፥6። ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥
እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው።
2መልካም ሰው ከጌታ ዘንድ ሞገስን ያገኛል፥
ተንኰለኛውን ሰው ግን ጌታ ይፈርድበታል።
3ክፋት ለሰው ዋስትና አያስገኝም፥
የጻድቃንን ሥር ግን ምንም አያንቀሳቅሰውም።
4ጐበዝ ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፥
አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።
5የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፥
የክፉዎች ምክር ግን ሽንገላ ነው።
6የክፉ ሰዎች ቃላት ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥
የቅኖች አፍ ግን ያድናቸዋል።
7ክፉ ሰዎች ይወድቃሉ፥ ፈጽሞም አይገኙም፥
የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
8ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥
ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
9ምግብ ሳይኖረው ከሚኮራ ሰው
አገልጋይ ኖሮት የተዋረደ ሰው ይሻላል።
10ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፥
የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።
11መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥
ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።
12ክፉ ሰዎች በክፉዎች ወጥመድ ይደሰታሉ፥
የጻድቃን ሥር ግን ፍሬን ያፈራል።
13ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፥
ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።
14የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥
ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል።
15የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት፥
ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።
16የሰነፍ ቁጣ ቶሎ ይታወቃል፥
ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።
17እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፥
የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል።
18እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፥
የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው።
19የእውነት ከንፈር ለዘለዓለም ትቆማለች፥
ውሸተኛ ምላስ ግን ለቅጽበት ነው።
20ክፉን በሚያስቡ ልብ ውስጥ ተንኰል አለ፥
በሰላም ለሚመክሩ ግን ደስታ አላቸው።
21ጻድቅን መከራ አያገኘውም፥
ኀጥኣን ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው።
22ውሸተኛ ከንፈር በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥
እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።
23ብልህ ሰው እውቀትን ይሸሽጋል፥
የሰነፎች ልብ ግን ስንፍናን ያወራል።
24የትጉ እጅ ትገዛለች፥
የታካች እጅ ግን ትገብራለች።
25ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል፥
መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።
26ጻድቅ ለባልንጀራው መንገዱን ያሳያል፥
የኀጥኣን መንገድ ግን ታስታቸዋለች።
27ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥
ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።
28በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ
በጎዳናዋም ሞት የለም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 12
12
1 #
ሲራ. 21፥6። ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥
እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው።
2መልካም ሰው ከጌታ ዘንድ ሞገስን ያገኛል፥
ተንኰለኛውን ሰው ግን ጌታ ይፈርድበታል።
3ክፋት ለሰው ዋስትና አያስገኝም፥
የጻድቃንን ሥር ግን ምንም አያንቀሳቅሰውም።
4ጐበዝ ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፥
አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።
5የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፥
የክፉዎች ምክር ግን ሽንገላ ነው።
6የክፉ ሰዎች ቃላት ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥
የቅኖች አፍ ግን ያድናቸዋል።
7ክፉ ሰዎች ይወድቃሉ፥ ፈጽሞም አይገኙም፥
የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
8ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥
ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
9ምግብ ሳይኖረው ከሚኮራ ሰው
አገልጋይ ኖሮት የተዋረደ ሰው ይሻላል።
10ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፥
የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።
11መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥
ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።
12ክፉ ሰዎች በክፉዎች ወጥመድ ይደሰታሉ፥
የጻድቃን ሥር ግን ፍሬን ያፈራል።
13ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፥
ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።
14የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥
ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል።
15የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት፥
ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።
16የሰነፍ ቁጣ ቶሎ ይታወቃል፥
ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።
17እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፥
የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል።
18እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፥
የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው።
19የእውነት ከንፈር ለዘለዓለም ትቆማለች፥
ውሸተኛ ምላስ ግን ለቅጽበት ነው።
20ክፉን በሚያስቡ ልብ ውስጥ ተንኰል አለ፥
በሰላም ለሚመክሩ ግን ደስታ አላቸው።
21ጻድቅን መከራ አያገኘውም፥
ኀጥኣን ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው።
22ውሸተኛ ከንፈር በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥
እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።
23ብልህ ሰው እውቀትን ይሸሽጋል፥
የሰነፎች ልብ ግን ስንፍናን ያወራል።
24የትጉ እጅ ትገዛለች፥
የታካች እጅ ግን ትገብራለች።
25ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል፥
መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።
26ጻድቅ ለባልንጀራው መንገዱን ያሳያል፥
የኀጥኣን መንገድ ግን ታስታቸዋለች።
27ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥
ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።
28በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ
በጎዳናዋም ሞት የለም።