መጽሐፈ ምሳሌ 8
8
1 #
ምሳ. 1፥20፤21። በውኑ ጥበብ አትጮኽምን?
ማስተዋልስ ድምፅዋን አታሰማምን?
2በኮረብታ ላይ በመንገድ አጠገብ
በጎዳና መካከል ትቆማለች።
3በበሮች አጠገብ በከተማይቱም መግቢያ፥
በደጆች መግቢያ ትጮኻለች፦
4“እናንተ ሰዎች፥ እናንተን እጠራለሁ፥
ድምፄም ወደ ሰዎች ልጆች ነው።
5እናንተ አላዋቂዎች፥ ማመዛዘንን ተረዱ፥
እናንተም ሞኞች አስተውሉ።
6ክቡር ነገርን እናገራለሁና ስሙ፥
ከንፈሮቼም ቅን ነገርን ለመናገር ይከፈታሉ።
7አፌ እውነትን ይናገራልና፥
ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ።
8የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ#8፥8 ቀጥተኛ፥ ትክክል፥ ግልጽ፥ ቅን። ናቸው፥
በውስጣቸውም ምንም ጠማማና ጠመዝማዛ ነገር የለም።
9እነርሱ ለሚያስተውል የቀኑ ናቸው፥
እውቀትንም ላገኟት ትክክል ናቸው።
10ተግሣጼን እንጂ ብርን አትቀበሉ፥
ከተመረጠ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ።
11 #
ሲራ. 24፥1-22። ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለችና
የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።
12እኔ ጥበብ፥ በብልሃት ተቀምጫለሁ፥
እውቀትንም ጥንቃቄንም አግኝቻለሁ።
13ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥
ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ
ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ።
14ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፥
ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ።
15ነገሥታት በእኔ ይነግሣሉ፥
ሹማምንትም የቀናውን ነገር ይደነግጋሉ።
16ባለ ሥልጣኖች በእኔ ይመራሉ፥
ክቡራን ምድርን ያስተዳድራሉ።
17እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥
ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።
18ብልጥግናና ክብር በእኔ ዘንድ ነው፥
ብዙ ሀብትና ጽድቅም።
19ፍሬዬም ከምዝምዝ ወርቅ ይሻላል፥
ቡቃያዬም ከተመረጠች ብር።
20እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥
በፍርድም ጎዳና መካከል፥
21ለሚወድዱኝ ርስት አወርሳቸው ዘንድ
ቤተ መዛግብታቸውንም እሞላ ዘንድ።
22 #
ሲራ. 1፥4፤9፤ ራእ. 3፥14። ጌታ የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥
በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ።
23ከጥንቱ ከዘለዓለም ጀምሮ ተሾምሁ
ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ።
24ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ ተወለድሁ፥
የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ።
25ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥
ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድሁ፥
26ምድሪቱንና ሜዳውን ገና ሳይፈጥር፥
የመጀመሪያውንም የዓለም አፈር።
27 #
ጥበ. 9፥9፤ ሲራ. 24፥3-6። ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥
በቀላያት ፊት ክበብን በደነገገ ጊዜ፥
28ደመናትን በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፥
የቀላይን ምንጮች ባጸና ጊዜ፥
29ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ
ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥
የምድርን መሠረት በመሠረተ ጊዜ፥
30የዚያን ጊዜ እኔ በእርሱ ዘንድ ዋና ሠራተኛ ነበርሁ፥
ዕለት ዕለት ደስ አሰኘው ነበርሁ፥
በፊቱም ሁልጊዜ ደስ ይለኝ ነበርሁ፥
31ደስታዬም በምድሩ
ተድላዬም በሰው ልጆች ነበረ።
32 #
ሲራ. 14፥20-27። አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥
መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው።
33ትምህርቴን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸል አትበሉትም።
34የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው
ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥
የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።
35እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና።
ከጌታም ሞገስን ያገኛልና።
36እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፥
የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 8
8
1 #
ምሳ. 1፥20፤21። በውኑ ጥበብ አትጮኽምን?
ማስተዋልስ ድምፅዋን አታሰማምን?
2በኮረብታ ላይ በመንገድ አጠገብ
በጎዳና መካከል ትቆማለች።
3በበሮች አጠገብ በከተማይቱም መግቢያ፥
በደጆች መግቢያ ትጮኻለች፦
4“እናንተ ሰዎች፥ እናንተን እጠራለሁ፥
ድምፄም ወደ ሰዎች ልጆች ነው።
5እናንተ አላዋቂዎች፥ ማመዛዘንን ተረዱ፥
እናንተም ሞኞች አስተውሉ።
6ክቡር ነገርን እናገራለሁና ስሙ፥
ከንፈሮቼም ቅን ነገርን ለመናገር ይከፈታሉ።
7አፌ እውነትን ይናገራልና፥
ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ።
8የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ#8፥8 ቀጥተኛ፥ ትክክል፥ ግልጽ፥ ቅን። ናቸው፥
በውስጣቸውም ምንም ጠማማና ጠመዝማዛ ነገር የለም።
9እነርሱ ለሚያስተውል የቀኑ ናቸው፥
እውቀትንም ላገኟት ትክክል ናቸው።
10ተግሣጼን እንጂ ብርን አትቀበሉ፥
ከተመረጠ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ።
11 #
ሲራ. 24፥1-22። ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለችና
የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።
12እኔ ጥበብ፥ በብልሃት ተቀምጫለሁ፥
እውቀትንም ጥንቃቄንም አግኝቻለሁ።
13ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥
ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ
ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ።
14ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፥
ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ።
15ነገሥታት በእኔ ይነግሣሉ፥
ሹማምንትም የቀናውን ነገር ይደነግጋሉ።
16ባለ ሥልጣኖች በእኔ ይመራሉ፥
ክቡራን ምድርን ያስተዳድራሉ።
17እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥
ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።
18ብልጥግናና ክብር በእኔ ዘንድ ነው፥
ብዙ ሀብትና ጽድቅም።
19ፍሬዬም ከምዝምዝ ወርቅ ይሻላል፥
ቡቃያዬም ከተመረጠች ብር።
20እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥
በፍርድም ጎዳና መካከል፥
21ለሚወድዱኝ ርስት አወርሳቸው ዘንድ
ቤተ መዛግብታቸውንም እሞላ ዘንድ።
22 #
ሲራ. 1፥4፤9፤ ራእ. 3፥14። ጌታ የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥
በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ።
23ከጥንቱ ከዘለዓለም ጀምሮ ተሾምሁ
ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ።
24ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ ተወለድሁ፥
የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ።
25ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥
ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድሁ፥
26ምድሪቱንና ሜዳውን ገና ሳይፈጥር፥
የመጀመሪያውንም የዓለም አፈር።
27 #
ጥበ. 9፥9፤ ሲራ. 24፥3-6። ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥
በቀላያት ፊት ክበብን በደነገገ ጊዜ፥
28ደመናትን በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፥
የቀላይን ምንጮች ባጸና ጊዜ፥
29ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ
ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥
የምድርን መሠረት በመሠረተ ጊዜ፥
30የዚያን ጊዜ እኔ በእርሱ ዘንድ ዋና ሠራተኛ ነበርሁ፥
ዕለት ዕለት ደስ አሰኘው ነበርሁ፥
በፊቱም ሁልጊዜ ደስ ይለኝ ነበርሁ፥
31ደስታዬም በምድሩ
ተድላዬም በሰው ልጆች ነበረ።
32 #
ሲራ. 14፥20-27። አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥
መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው።
33ትምህርቴን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸል አትበሉትም።
34የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው
ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥
የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።
35እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና።
ከጌታም ሞገስን ያገኛልና።
36እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፥
የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።”