መዝሙረ ዳዊት 138
138
1የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 9፥1። አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥
በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።
2ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፥
ስለ ጽኑ ፍቅርሀና ስለ ታማኝነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥
በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህንና ቃልህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
3በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፥
ነፍሴን በኃይልህ አጸናሃት።
4አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፥
የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።
5በጌታም መንገድ ይዘምራሉ፥
የጌታ ክብር ታላቅ ነውና።
6 #
ሉቃ. 1፥51-52። ጌታ ከፍ ያለ ነውና፥
ዝቅተኞችን ይመለከታልና፥
ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ያውቃል።
7በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፥
በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥
ቀኝህም ታድነኛለች።
8ጌታ ብድራትን ይመልስልኛል፥
አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ለዘለዓለም ነው፥
አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 138: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 138
138
1የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 9፥1። አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥
በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።
2ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፥
ስለ ጽኑ ፍቅርሀና ስለ ታማኝነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥
በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህንና ቃልህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
3በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፥
ነፍሴን በኃይልህ አጸናሃት።
4አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፥
የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።
5በጌታም መንገድ ይዘምራሉ፥
የጌታ ክብር ታላቅ ነውና።
6 #
ሉቃ. 1፥51-52። ጌታ ከፍ ያለ ነውና፥
ዝቅተኞችን ይመለከታልና፥
ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ያውቃል።
7በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፥
በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥
ቀኝህም ታድነኛለች።
8ጌታ ብድራትን ይመልስልኛል፥
አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ለዘለዓለም ነው፥
አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።