የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 139

139
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።
2 # 2ነገ. 19፥27፤ ኢዮብ 12፥3። አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፥
ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።
3ጉዞዬንና መኝታዬን አንተ መረመርህ፥
መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥
4የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።
5ከኋላና ከፊት ጠበቅኸኝ፥
እጅህንም በላዬ አደረግህ።
6 # መዝ. 131፥1። እውቀትህ እጅጉን ያስደንቃል፥
ከከፍታውም ብዛት ልደርስበት አልችልም።
7ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ?
ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
8 # ኢዮብ 23፥8-9፤ ኤር. 23፥23-24። ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ።
ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።
9የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥
እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥
10በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥
ቀኝህም ትይዘኛለች።
11በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥
በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ቢሆን፥
12 # ኢዮብ 12፥22። ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥
ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፥
እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።
13 # ጥበ. 7፥1፤ መክ. 11፥5፤ ኢዮብ 1፥21። አቤቱ፥ አንተ ኩላሊቴን#139፥13 የሰውነቴን የውስጥ ክፍሎች። ፈጥረሃልና፥
በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።
14ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፥
ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
15እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥
አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ
አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም።
16 # ሚል. 3፥16። ያልተሠራ አካሌን ዐይኖችህ አዩ፥
የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ
አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።
17 # ሲራ. 18፥5-7። አቤቱ፥ ሐሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደምን እጅግ የተከበሩ ናቸው!
ቁጥራቸውም እንደምን በዛ!
18 # ኢዮብ 11፥7። ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፥
ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ።
19 # ኢዮብ 21፥14። አቤቱ፥ አንተ ክፉዉን የምትገድል ከሆንህስ፥
የደም ሰዎች ሆይ፥ “ከእኔ ፈቀቅ በሉ”።
20በክፋት ይናገሩብሃልና፥
ጠላቶችህም በከንቱ ያምፁብሃል።
21 # መዝ. 119፥158። አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን?
በአንተ ላይ የሚነሡትንም አልናቅሁምን?
22ጨርሶ ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ።
23 # መዝ. 17፥3፤ 26፥2። አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፥
ፈትነኝ መንገዴንም እወቅ፥
24በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፥
የዘለዓለምንም መንገድ ምራኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ