መዝሙረ ዳዊት 148
148
1ሃሌ ሉያ።
ጌታን ከሰማያት አመስግኑት፥
በአርያም አመስግኑት።
2 #
መዝ. 103፥20፤ ዳን. 3፥58-63። መላእክቱ ሁሉ፥ አመስግኑት፥
ሠራዊቱ ሁሉ፥ አመስግኑት።
3ፀሐይና ጨረቃ፥ አመስግኑት፥
የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ፥ አመስግኑት።
4ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት፥
ከሰማያት በላይ ያላችሁም ውኃዎችም እንዲሁ።
5 #
መዝ. 33፥9፤ ዘፍ. 1፥3፤ ዮዲ. 16፥14። የጌታን ስም ያመስግኑት፥
እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ።
6ለዘለዓለም ዓለም አቆማቸው፥
ትእዛዝን ሰጠ፥ አያልፉትምም።
7 #
መዝ. 135፥6፤ ዘፍ. 1፥21። የባሕር አራዊትና ጥልቆችም ሁሉ፥
ጌታን ከምድር አመስግኑት፥
8እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥
ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥
9 #
ኢሳ. 44፥23። ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፥
የሚያፈራም ዛፍና ዝግባ ሁሉ፥
10 #
መዝ. 30፥5፤ ዘፍ. 1፥21፤24፤ ዘዳ. 4፥7። አራዊትና እንስሳት ሁሉ፥
የሚሳቡና የሚበርሩ ወፎችም፥
11የምድር ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥
አለቆችና የምድር ፈራጆች ሁሉ፥
12ጉልማሶችና ልጃገረዶች፥
ሽማግሌዎችና ልጆች፥
13 #
መዝ. 30፥5፤ ዘዳ. 4፥7። የጌታን ስም ያመስግኑ፥
ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥
ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው።
14የሕዝቡንም ቀንድ#148፥14 ኃይል ከፍ ከፍ ያደርጋል፥
የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና
ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 148: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 148
148
1ሃሌ ሉያ።
ጌታን ከሰማያት አመስግኑት፥
በአርያም አመስግኑት።
2 #
መዝ. 103፥20፤ ዳን. 3፥58-63። መላእክቱ ሁሉ፥ አመስግኑት፥
ሠራዊቱ ሁሉ፥ አመስግኑት።
3ፀሐይና ጨረቃ፥ አመስግኑት፥
የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ፥ አመስግኑት።
4ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት፥
ከሰማያት በላይ ያላችሁም ውኃዎችም እንዲሁ።
5 #
መዝ. 33፥9፤ ዘፍ. 1፥3፤ ዮዲ. 16፥14። የጌታን ስም ያመስግኑት፥
እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ።
6ለዘለዓለም ዓለም አቆማቸው፥
ትእዛዝን ሰጠ፥ አያልፉትምም።
7 #
መዝ. 135፥6፤ ዘፍ. 1፥21። የባሕር አራዊትና ጥልቆችም ሁሉ፥
ጌታን ከምድር አመስግኑት፥
8እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥
ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥
9 #
ኢሳ. 44፥23። ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፥
የሚያፈራም ዛፍና ዝግባ ሁሉ፥
10 #
መዝ. 30፥5፤ ዘፍ. 1፥21፤24፤ ዘዳ. 4፥7። አራዊትና እንስሳት ሁሉ፥
የሚሳቡና የሚበርሩ ወፎችም፥
11የምድር ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥
አለቆችና የምድር ፈራጆች ሁሉ፥
12ጉልማሶችና ልጃገረዶች፥
ሽማግሌዎችና ልጆች፥
13 #
መዝ. 30፥5፤ ዘዳ. 4፥7። የጌታን ስም ያመስግኑ፥
ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥
ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው።
14የሕዝቡንም ቀንድ#148፥14 ኃይል ከፍ ከፍ ያደርጋል፥
የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና
ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ሃሌ ሉያ።