መዝሙረ ዳዊት 32
32
1የዳዊት ትምህርት።
#
ኢሳ. 1፥18፤ መዝ. 65፥3፤ ሮሜ 4፥7-8። መተላለፉ ይቅር የተባለችለት፥
ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው።
2ጌታ በደልን የማይቈጥርበት
በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ብፁዕ ነው።
3 #
መዝ. 31፥11። ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ
ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ፥
4በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥
ጉልበቴ በበጋ ትኩሳት ዛለ።
5 #
መዝ. 38፥19፤ 51፥5። ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥
በደሌንም አልሸፈንሁም፥
መተላለፌን ለጌታ እነግራለሁ አልሁ፥
አንተም የኃጢአቴን ሸክም ተውህልኝ።
6 #
መዝ. 18፥5። ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ
ወደ አንተ ይለምናል፥
ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም።
7አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥
ከጭንቅ ትጠብቀኛለህ፥
ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።
8አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፥
ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።
9ወደ አንተ እንዳይቀርቡ
በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሙአቸው፥
ልብ እንደሌላቸው
እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
10በኃጢአተኛ ብዙ መቅሠፍት አለበት፥
በጌታ የሚታመነውን ግን ምሕረት ይከብበዋል።
11 #
መዝ. 33፥1። ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፥
ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ እልል በሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 32: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ