መዝሙረ ዳዊት 33
33
1የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 32፥11፤ 147፥1። ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ፥
ለቅኖች ምስጋና ይገባል።
2 #
መዝ. 92፥4፤ 144፥9። ጌታን በመሰንቆ አመስግኑት፥
ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።
3አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥
በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፥
4የጌታ ቃል ቅን ነውና
ሥራውም ሁሉ የታመነ ነውና።
5 #
መዝ. 119፥64። ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፥
የጌታ ቸርነት ምድርን ሞላች።
6 #
ዘፍ. 2፥1። በጌታ ቃል ሰማዮች ጸኑ፥
በአፉም እስትንፋስ ሠራዊታቸው#33፥6 ፀሐይ፥ ጨረቃና ከዋክብት ተፈጠረ፥
7 #
መዝ. 78፥13፤ ዘፍ. 1፥9-10፤ ዘፀ. 15፥8፤ ኢያ. 3፥16። የባሕርን ውኃ በኰዳ የሚሰበስበው፥
ቀላዮችንም በመዝገቦች የሚያኖራቸው።
8ምድር ሁሉ ጌታን ትፍራው፥
በዓለም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ።
9 #
መዝ. 148፥5፤ ዘፍ. 1፥3፤ ዮዲ. 16፥14። እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፥
እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።
10ጌታ የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥
የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።
11 #
ምሳ. 19፥21፤ ኢሳ. 40፥8። የጌታ ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥
የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
12 #
መዝ. 144፥15፤ ዘፀ. 19፥6፤ ዘዳ. 7፥6። ጌታ አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥
እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።
13 #
ኢዮብ 34፥21፤ ሲራ. 15፥19፤ ኤር. 16፥17፤ 32፥19። ጌታ ከሰማይ ተመለከተ፥
የሰውንም ልጆች ሁሉ አየ።
14ከማደሪያው ቦታ ሆኖ
በምድር ወደሚኖሩ ሁሉ ተመለከተ፥
15እርሱ ብቻውን ልባቸውን የሠራ
ሥራቸውንም ሁሉ የሚያስተውል።
16 #
ዮዲ. 9፥7፤ 1መቃ. 3፥19። ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥
ኃያልም በጉልበቱ አያመልጥም።
17ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፥
በኃይሉም ብዛት አያስመልጥም።
18እነሆ፥ የጌታ ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥
በቸርነቱም ወደሚታመኑ፥
19ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ፥
በራብም ጊዜ በሕይወት ይጠብቃቸው ዘንድ።
20 #
መዝ. 115፥9። ነፍሳችን ጌታን ተስፋ ታደርገዋለች፥
ረዳታችንና ጋሻችን እርሱ ነውና።
21ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥
በቅዱስ ስሙም ታምነናልና።
22አቤቱ፥ ቸርነትህ በላያችን ትሁን፥
በአንተ እንደ ታመንን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 33: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ