መዝሙረ ዳዊት 35
35
1የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ የሚከሱኝን ክሰሳቸው፥
የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።
2ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥
እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
3ሰይፍንና ጦርን ምዘዝ፥
የሚያሳድዱኝን ለመቃወም፥
ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።
4 #
መዝ. 40፥15፤ 71፥13። ነፍሴን ሊያጠፉ የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቁሉም፥
ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይዋረዱ
ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
5 #
መዝ. 1፥4፤ 83፥14፤ ኢዮብ 21፥18። በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፥
የጌታም መልአክ ያስጨንቃቸው።
6መንገዳቸው ዳጥና ጨለማ ይሁን፥
የጌታም መልአክ ያሳድዳቸው።
7በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥
ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና።
8 #
መዝ. 7፥16፤ 9፥16፤ 57፥7፤ ምሳ. 26፥27፤ መክ. 10፥8፤ ሲራ. 27፥26። ያላወቁት ወጥመድ ይምጣባቸው፥
የሸሸጉትም ወጥመድ ይያዛቸው፥
በዚህ ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ።
9ነፍሴ ግን በጌታ ደስ ይላታል፥
በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።
10 #
መዝ. 86፥8፤ 89፥7፤ 9፤ ዘፀ. 15፥11። አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው?
ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥
ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።
11የሐሰት ምስክሮች ተነሡብኝ፥
የማላውቀውንም በእኔ ላይ ተናገሩ።
12 #
መዝ. 27፥12፤ 38፥20-21፤ 109፥5፤ ኤር. 18፥20። በበጎ ፈንታ ክፋትን መለሱልኝ፥
ለብቻዬም ቀረሁ።
13እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥
ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፥
ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ።
14ለወዳጄና ለወንድሜ እንደማደርግ አደረግሁ፥
ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ።
15በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው፥
ግፈኞች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላወቅሁም፥
መቦጫጨቃቸውን አላቆሙም።
16ፈተኑኝ በሣቅም ዘበቱብኝ፥
ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቀጩ።
17 #
መዝ. 17፥12፤ 22፥22፤ 58፥7። አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ዝም ብለህ ታየኛለህ?
ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው
ብቸኛዪቱንም ከአንበሶች አድናት።
18 #
መዝ. 22፥23፤ 26፥12፤ 35፥18፤ 40፥10፤ 149፥1። አቤቱ፥ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እገዛልሃለሁ፥
በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንሃለሁ።
19 #
መዝ. 38፥17። ከሐዲ ጠላቶቼ በእኔ ደስ አይበላቸው፥
በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጠቃቀሱብኝ።
20 #
መዝ. 120፥6-7። በእርጋታ በምድሪቱ ለተቀመጡት ሰላምን አይናገሩምና፥
በቁጣም ሽንገላን ይመክራሉ።
21 #
መዝ. 40፥16፤ ሰቆ.ኤ. 2፥16። አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ፥
እሰይ እሰይ፥ ዓይናችን አየው ይላሉ።
22 #
መዝ. 22፥12፤ 38፥21፤ 109፥1። አቤቱ፥ አንተ አየኸው፥ ዝም አትበል፥
አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ።
23አምላኬ ጌታዬም፥ ትፈርድልኝ ዘንድ ተነሥ፥
አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ።
24አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፥
በእኔም ምክንያት ደስ አይበላቸው።
25በልባቸው፦ እሰይ እሰይ፥ ነፍሳችንን ደስ አላት አይበሉ፥
ደግሞም፦ ዋጥነው አይበሉ።
26በመከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፥
በአንድነትም ይጐስቁሉ፥
በእኔ ላይ የሚታበዩ እፍረትንና ጉስቁልናን ይልበሱ።
27ጽድቄን የሚወድዱአት ደስ ይበላቸው
ሐሴትንም ያድርጉ፥
የባርያውን ሰላም የሚወድድ ጌታ
ታላቅ ይሁን ዘወትር ይበሉ።
28 #
መዝ. 71፥15-16። ምላሴ ጽድቅህን
ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 35: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 35
35
1የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ የሚከሱኝን ክሰሳቸው፥
የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።
2ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥
እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
3ሰይፍንና ጦርን ምዘዝ፥
የሚያሳድዱኝን ለመቃወም፥
ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።
4 #
መዝ. 40፥15፤ 71፥13። ነፍሴን ሊያጠፉ የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቁሉም፥
ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይዋረዱ
ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
5 #
መዝ. 1፥4፤ 83፥14፤ ኢዮብ 21፥18። በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፥
የጌታም መልአክ ያስጨንቃቸው።
6መንገዳቸው ዳጥና ጨለማ ይሁን፥
የጌታም መልአክ ያሳድዳቸው።
7በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥
ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና።
8 #
መዝ. 7፥16፤ 9፥16፤ 57፥7፤ ምሳ. 26፥27፤ መክ. 10፥8፤ ሲራ. 27፥26። ያላወቁት ወጥመድ ይምጣባቸው፥
የሸሸጉትም ወጥመድ ይያዛቸው፥
በዚህ ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ።
9ነፍሴ ግን በጌታ ደስ ይላታል፥
በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።
10 #
መዝ. 86፥8፤ 89፥7፤ 9፤ ዘፀ. 15፥11። አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው?
ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥
ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።
11የሐሰት ምስክሮች ተነሡብኝ፥
የማላውቀውንም በእኔ ላይ ተናገሩ።
12 #
መዝ. 27፥12፤ 38፥20-21፤ 109፥5፤ ኤር. 18፥20። በበጎ ፈንታ ክፋትን መለሱልኝ፥
ለብቻዬም ቀረሁ።
13እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥
ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፥
ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ።
14ለወዳጄና ለወንድሜ እንደማደርግ አደረግሁ፥
ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ።
15በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው፥
ግፈኞች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላወቅሁም፥
መቦጫጨቃቸውን አላቆሙም።
16ፈተኑኝ በሣቅም ዘበቱብኝ፥
ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቀጩ።
17 #
መዝ. 17፥12፤ 22፥22፤ 58፥7። አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ዝም ብለህ ታየኛለህ?
ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው
ብቸኛዪቱንም ከአንበሶች አድናት።
18 #
መዝ. 22፥23፤ 26፥12፤ 35፥18፤ 40፥10፤ 149፥1። አቤቱ፥ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እገዛልሃለሁ፥
በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንሃለሁ።
19 #
መዝ. 38፥17። ከሐዲ ጠላቶቼ በእኔ ደስ አይበላቸው፥
በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጠቃቀሱብኝ።
20 #
መዝ. 120፥6-7። በእርጋታ በምድሪቱ ለተቀመጡት ሰላምን አይናገሩምና፥
በቁጣም ሽንገላን ይመክራሉ።
21 #
መዝ. 40፥16፤ ሰቆ.ኤ. 2፥16። አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ፥
እሰይ እሰይ፥ ዓይናችን አየው ይላሉ።
22 #
መዝ. 22፥12፤ 38፥21፤ 109፥1። አቤቱ፥ አንተ አየኸው፥ ዝም አትበል፥
አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ።
23አምላኬ ጌታዬም፥ ትፈርድልኝ ዘንድ ተነሥ፥
አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ።
24አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፥
በእኔም ምክንያት ደስ አይበላቸው።
25በልባቸው፦ እሰይ እሰይ፥ ነፍሳችንን ደስ አላት አይበሉ፥
ደግሞም፦ ዋጥነው አይበሉ።
26በመከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፥
በአንድነትም ይጐስቁሉ፥
በእኔ ላይ የሚታበዩ እፍረትንና ጉስቁልናን ይልበሱ።
27ጽድቄን የሚወድዱአት ደስ ይበላቸው
ሐሴትንም ያድርጉ፥
የባርያውን ሰላም የሚወድድ ጌታ
ታላቅ ይሁን ዘወትር ይበሉ።
28 #
መዝ. 71፥15-16። ምላሴ ጽድቅህን
ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል።