የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 44

44
1ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።
2 # መዝ. 78፥3። አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥
አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
3 # መዝ. 78፥55። እጅህ አሕዛብን አባረረች፥ እነርሱንም ተከልህ፥
አሕዛብን አስጨንቀህ እነሱን አለመለምክ።
4 # ዘኍ. 6፥25፤ ዘዳ. 8፥17፤ ኢያ. 24፥12፤ መዝ. 4፥7፤ 31፥17፤ 67፥2፤ 80፥4፤ ዳን. 9፥17። በሰይፋቸው ምድርን አልወረሱም
ክንዳቸውም አላዳናቸው፥
ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፥
ወድደሃቸዋልና።
5 # መዝ. 145፥1። አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፥
ለያዕቆብ መድኃኒትን እዘዝ።
6በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥
በስምህም የሚነሡብንን እንረግጣለን።
7በቀስቴ የምታመን አይደለሁምና፥
ሰይፌም አያድነኝምና፥
8አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን፥
የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው።
9ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን፥
ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
10 # መዝ. 89፥39-52። አሁን ግን ጣልከን አሳፈርኸንም፥
ከሠራዊታችንም ጋር አትወጣም።#መዝ. 60፥12።
11 # ዘሌ. 26፥17፤ ዘዳ. 28፥25። ከጠላቶቻችንም ፊት ወደ ኋላችን መለስኸን፥
የሚጠሉንም ተነጣጠቁን።
12 # ዘሌ. 26፥33፤ ዘዳ. 28፥64። እንደ በጎች ሊበሉን ሰጠኸን፥
ወደ አሕዛብም በተንኸን።
13 # ዘዳ. 32፥30፤ ኢሳ. 52፥3። ሕዝብህን ያለ ዋጋ ሰጠህ፥
በመለወጣቸውም ትርፍ የለም።
14 # መዝ. 79፥4፤ 80፥7፤ 123፥3-4፤ ኢዮብ 12፥4፤ ዳን. 9፥16። ለጎረቤቶቻችን ስድብ፥
በዙሪያችንም ላሉ መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።
15በአሕዛብ ዘንድ ምሳሌ፥
በሕዝብም ዘንድ መናቂያ አደረግኸን።
16ጉስቁልናዬ ሁልጊዜ በፊቴ ነው፥
የፊቴም እፍረት ሸፈነኝ።
17ከሚሳደብና ከሚላገድ ቃል የተነሣ፥
ከጠላትና ከቂመኛ ፊት የተነሣ ነው።
18ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥ አልረሳንህም፥
ኪዳንህንም አልወነጀልንም።
19ልባችን ወደ ኋላው አልተመለሰም፥
ፍለጋችንም ከመንገድህ ፈቀቅ አላለም፥
20 # ኤር. 9፥10። በክፉ ስፍራ አዋርደኸናልና፥
በሞት ጥላም ሰውረኸናልና።
21የአምላካችንን ስም ረስተንስ ቢሆን፥
እጃችንንም ወደ ሌላ አምላክ አንሥተንስ ቢሆን፥
22እግዚአብሔር ይህንን አይመረምርም ነበርን?
እርሱ ልብ የሰወረውን ያውቃልና።
23 # ሮሜ 8፥36። ስለ አንተ ሁልጊዜ ተገድለናል፥
እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።
24 # መዝ. 10፥1፤ 74፥1፤ 77፥8፤ 79፥5፤ 83፥2። አቤቱ፥ ንቃ፥ ለምንስ ትተኛለህ?
ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን።
25 # መዝ. 10፥11፤ 89፥47፤ ኢዮብ 13፥24። ለምንስ ፊትህን ትሰውራለህ?
መከራችንንና ጭንቃችንን ለምን ትረሳለህ?
26 # መዝ. 119፥25። ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቁላለችና፥
ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቃለችና።
27አቤቱ፥ ተነሥና እርዳን፥
ስለ ጽኑ ፍቅርህም ተቤዠን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ