መዝሙረ ዳዊት 5
5
1ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 86፥6፤ 130፥1-2። አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥
መቃተቴንም አስተውል፥
3የጩኸቴን ድምፅ አድምጥ፥
ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥
አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
4 #
ጥበ. 16፥28። በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥
በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም።
5አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፥
ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።
6በከንቱ የሚመኩ በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፥
ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
7 #
መዝ. 101፥7፤ ጥበ. 14፥9፤ ዕብ. 1፥13። ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፥
ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው ጌታ ይጸየፋል።
8 #
መዝ. 138፥2፤ ዮናስ 2፥5። እኔ ግን በቸርነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፥
አንተን በመፍራት ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
9 #
መዝ. 23፥3፤ ምሳ. 4፥11፤ ኢሳ. 26፥7። አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥
መንገዴን በፊትህ አቅና።
10 #
ሮሜ 3፥13። በአፋቸው እውነት የለምና፥
ልባቸውም ከንቱ ነው፥
ጉሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥
በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
11 #
መዝ. 141፥10። አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፥
ስለ ክፋታቸውም ብዛት አስወግዳቸው፥
እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
12 #
መዝ. 64፥11። በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ሐሴትን ያድርጉ፥
ለዘለዓለሙ በደስታ ይዘምሩ፥ እነርሱንም ትጠብቃቸዋለህ፥
ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይደሰቱ።
13አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፥
አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 5: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 5
5
1ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 86፥6፤ 130፥1-2። አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥
መቃተቴንም አስተውል፥
3የጩኸቴን ድምፅ አድምጥ፥
ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥
አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
4 #
ጥበ. 16፥28። በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥
በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም።
5አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፥
ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።
6በከንቱ የሚመኩ በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፥
ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
7 #
መዝ. 101፥7፤ ጥበ. 14፥9፤ ዕብ. 1፥13። ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፥
ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው ጌታ ይጸየፋል።
8 #
መዝ. 138፥2፤ ዮናስ 2፥5። እኔ ግን በቸርነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፥
አንተን በመፍራት ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
9 #
መዝ. 23፥3፤ ምሳ. 4፥11፤ ኢሳ. 26፥7። አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥
መንገዴን በፊትህ አቅና።
10 #
ሮሜ 3፥13። በአፋቸው እውነት የለምና፥
ልባቸውም ከንቱ ነው፥
ጉሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥
በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
11 #
መዝ. 141፥10። አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፥
ስለ ክፋታቸውም ብዛት አስወግዳቸው፥
እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
12 #
መዝ. 64፥11። በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ሐሴትን ያድርጉ፥
ለዘለዓለሙ በደስታ ይዘምሩ፥ እነርሱንም ትጠብቃቸዋለህ፥
ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይደሰቱ።
13አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፥
አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።