መዝሙረ ዳዊት 52
52
1ለመዘምራን አለቃ የዳዊት ትምህርት። 2#1ሳሙ. 21፥8፤ 22፥6።ኤዶማዊው ዶይቅ መጥቶ ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቷል ብሎ በነገረው ጊዜ፥
3ኃያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኩራራለህ?
ሁልጊዜስ በመተላለፍ?
4 #
መዝ. 12፥3፤ 59፥8፤ 120፥2-3፤ ሲራ. 51፥3። አንደበትህ ጥፋትን ያስባል፥
እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።
5 #
ኤር. 4፥22፤ ዮሐ. 3፥19-20። ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥
ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ።
6 #
ኤር. 9፥4። የሚያጠፋ ቃልን ሁሉ፥ የሽንገላ ምላስን ወደድህ።
7 #
መዝ. 27፥13፤ 28፥5፤ 56፥14፤ ኢዮብ 18፥14፤ ምሳ. 2፥22፤ ኢሳ. 38፥11። ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፥
ከድንኳንም ይነቅልሃል ያፈልስሃልም፥
ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
8 #
መዝ. 44፥14፤ 64፥9። ጻድቃን አይተው ይፈራሉ፥
በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦
9 #
ኢዮብ 31፥24፤ ምሳ. 11፥28። እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥
በሀብቱም ብዛት የታመነ፥
በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እነሆ።
10 #
መዝ. 1፥3፤ 92፥12-14፤ ኤር. 11፥16፤ 17፥8። እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፥
ለዓለምና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ርኅራኄ ታመንሁ።
11 #
መዝ. 22፥23፤ 26፥12፤ 35፥18፤ 149፥1። አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥
በቅዱሳንህም ዘንድ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 52: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ